መሪዎች በህዝቦቻቸው ዘንድ ተወዳጅ እና ተቀባይ ለመሆን እነኚህን ጥቂት ነጥቦች በትኩረት ማየት ይኖርባቸዋል።
1. Listen to the Public
(
ህዝብን ማዳመጥ: ከዜጎች ጋር መቀራረብ፣ ሃሳባቸውን እና ስጋታቸውን በትክክል ማጤን ያስፈልጋል።
እንዲሁም መተማመንን መፍጠር እና መቀራረብን ማጎልበት።
**
2. Transparent Communication
ግልጽ ግንኙነት ያስፈልጋል።
ይኸውም ስለ ውሳኔዎች፣ ስለ ፖሊሲዎች እና ተግዳሮቶች ግልጽ መሆን የታማኝነት እና የተጠያቂነት ስሜት ይፈጥራል።
3. Prioritize Education and Health:
ለትምህርት እና ለጤና ቅድሚያ መስጠት፡-
ጥራት ባለው ትምህርት እና ጤና ላይ ኢንቨስት ማድረግ የሰዎችን ህይወት በእጅጉ ሊያሻሽል ስለሚችል መሪዎችን በህዝቦች ዘንድ የበለጠ ተወዳጅ ያደርጋቸዋል።
4. Economic Opportunities:
የኢኮኖሚ እድሎችን መፍጠር:-
የስራ እድሎችን ለህዝብ መፍጠር፣ የሀገር ውስጥ የንግድ እንቅስቃሴ ማበረታታት፣ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን እንዲያሻሽሉ እድሉን ማመቻቸት መንግስትን በዜጎች ዘንድ እንዲወደድ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
5. Social Justice and Equality:
ማህበራዊ ፍትህ እና እኩልነት፡-
ፍትሃዊነትን ማሳደግ እና ማህበራዊ ጉዳዮችን መፍታት ከዜጎች ጋር ጥልቅ ስሜት እንዲኖር ያደርጋል። አንዱን አስደስቶ አንዱን ማስለቀስ አካታችነት የጎደለው፣ ፍትህ ያልታከለበት ስርአት ነው። እድሜም አይኖረውም።
6. Environmental Responsibility:
የአካባቢ ኃላፊነት፡-
ስለ ስርአትና አስተዳደር እያወራን ተፈጥሯዊ ሀብታችንን መዘንጋት የለብንም።
እናም መንግስትበበአየር ንብረት ለውጥ ላይ ርምጃ መውሰድ ወሳኝ ሚናው መሆን አለበት።
እናም የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ እንክብካቤን ያሳያል።
በእነዚህ ዘርፎች ላይ በማተኮር መሪዎች ከህዝቦቻቸው ጋር አዎንታዊ ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ!
**