ማሰብ ስታቆም ማመን ትጀምራለህ
"A life without reasoning is unworthy of man"
አንዳንዶች ፍልስፍና በዘመናችን እምብዛም የሚወደድ ሆኖ አለመገኘት ብቻ ሳይሆን እየተጠላም ነው ይላሉ፡፡
ሶቅራጥስ ራሱን አሳልፎ የሰጠላት ፕሌቶም ፍልስፍናን ከማጣት ይልቅ ሞት ይሻላል በማለት ሁለት ጊዜ መስዋዕት ሆኖ የቀረበላት ጳጳሳት ተከታዮችዋን ያሰሩባት ያሰቃዩባት... ይህች «ፍልስፍና» «ለመሆኑ ምን ብታነሳ ነው ይህ ሁሉ የመጣባት?» ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው
ተከታዮቿ የፍልስፍና ትልቁና የመጀመሪያ ጥያቄዋ «እውነት» ስለሆነ ነው ይላሉ «እውነት ምንድ ነው?» የሚለው ጥያቄ ፍልስፍና የተጣለችበት መሠረት ነው "በእርግጥ የምናየውን ነገር የምናየው የምንሰማውን ነገር የምንስማው የምናሸተውን ነገር የምናሸተው የምንነካውን ነገር የምንነካው...እውነት ስለሆነ ነው? ወይስ እውነት ነው ብለን ስለምናስብ?" በማለት ፈላስፎቹ ይጠይቃሉ
ይኸ ዓለም «ለእያንዳንዱ ሰው እምነቱ የእሱ እውነት ነው» ይለናል፡፡ «እምነትህ እውነት ነው›› በሚለው በዚህ ዓለም ውስጥ ፈላስፎቹ ደግሞ «ማስረጃ ማቅረብ የማትችልበት እምነት እውነት ሊሆን አይችልም» ይላሉ።
ታላቁ ፈላስፋ ፍሬዴሪክ ኒቼ «የምታምነው ለመኖሩ ማስረጃ ማቅረብ ካልቻልክ እምነትህ ውሸት ነው አባቴ ለእኔ ያስተላለፈው እምነት አያቴ የነገረውን ነው አያቴም የቅድም አያቴን ይዞ ለአባቴ አስተላለፈው እንግዲህ እኔ የምኖርበት እምነት አስቀድሞ ሌሎች የኖሩበትን እንጂ እኔ በማስረጃ አረጋግጬ ያገኘሁት አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለእምነትህ ማስረጃ የለህምና ውሸት ነው›› ይላል፡፡ ሌሎችም ፈላስፎች በዚህ ይስማማሉ፡፡
እንግዲህ ወደ «እውነት» ጥያቄ ስንመጣ ኒቼ ሊነሳ የሚገባው ፈላስፋ ይሆናል፡፡ እንደኒቼ እምነት «እውነት በተገቢ ሁኔታ የተነሳችበት የተጠየቀችበት በአንድ ሰውና በእንድ ቦታ ብቻ ነው ይኸውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እሱም በጲላጦስ ነው» ይላል፡፡ አናቶሊ ፍራንስም በዚህ አባባል «እስማማለሁ ብቻ ሳይሆን አምንበታለሁም» ይላል።
«ጲላጦስም እንግዲህ ንጉሥ ነህን? አለው:: ኢየሱስም መልሶ እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ እኔ ለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው፡፡ ጲላጦስም እውነት ምንድር ነው? አለው»
ዮሐ 17:38
እንግዲህ ጲላጦስ በጥያቄ የጀመራትን «እውነት» ለመመለስ የመጀመሪያ ሞካሪዎች ነገር ግን በሚገባ ያልመለሱት በመባል የሚነቀፉት ሶፊስቶች (Sophists) ናቸው::
«ስለ እውነት ለማወቅ ከስሜት እንነሳ» ይላሉ (ይኸን አባባላቸውን ሌሎቹ ፈላስፎች ለጆሮ የሻገተ ጩኸት ነው ይሉታል)፡፡ «እውነት የሚመጣው ከስሜት ነው፤ ስለዚህም የእውነት ጥያቄ (በሌላ ኣባባል ለጲላጦስ ጥያቄ መልሱ) ስሜትህ ነው» ይላሉ፡፡ «ስለዚህም እውነት ማለት የምትቀምሰው፣ የምታሽተው ፣ የምትነካው፣ የምትሰማውና የምታየው ነገር ነው» ማለት ነው በዚህ መልስ መጀመሪያ አለመስማማቱን የገለፀው ፕሌቶ ነበር።
«እውነት ማለት ሶፊስቶች እንደሚሉት ስሜትህ ከሆነ እውነት የለም ማለት ነው» ይለናል። «ምነው?» ሲሉት «ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው አንድን ነገር የሚያሸተው፣ የሚነካው፣ የሚቀምሰው...በተለያየ መንገድ ነውና» ባይ ነው።
"አንድን ነገር ሁለት ሰው በሁለት መንገድ ከሰማው ወይም ካየው ነገሩ አንድ መሆኑ አብቅቶዋል፤ ስለዚህም ነገሩ በራሱ እውነት አይደለም» ነው አባባሉ።
"ስለሆነም የእውነት ጥያቄ የሚመለሰው በምክንያታዊ ማሰብ (Reasoning) እንጂ በስሜት አይደለም" ይላል። «አንድን ነገር ለማየት ማሰብ ያስፈጋል። አስቀድመህ የምታስበው ነገር ወደ አይንህ መልዕክት አስተላልፎ የምታየውን ማየት ቻልክ በሌላ አባባል የምታየው እውነት መሆኑን የምታውቀው በማሰብህ ነው ስለዚህ እውነት ማለት "ማሰብ" ነው» ይላል፡፡
ይኸን የፕሌቶን አባባል የተስማማበት አሪስቶትል ነበር፡፡ በዚህም ላይ ተመስርቶ «የማሰብ ሕግ» (Laws of Reasoning) የሚል አወጣ፡፡ «በዚህ ዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ነገር እውነት የሚሆነው በመታየት በመነካት ወዘተ ሳይሆን ስለነገሩ በሚኖረን ሐሳብ ነው» ማለት ይሆናል፡፡
እዚህ ላይ እንደ ፊሮ ዓይነቶቹ ታላላቅ ጠርጣሪ ፈላስፎች ተነሱና «አንድን ነገር ሁልጊዜ እውነት የሚያደርገው ስለነገሩ ማሰብ ስለቻልን አይደለም» ይላሉ፡፡ በተለይም ፊሮ የአሪስቶትልን የማሰብ ሕግ» ሲያጣጥል «እንግዲህ አንድን ነገር እውነት የሚያደርገው ማሰብ ስለቻልን ከሆነ ሰው የሚያስብ ፍጡር ነው ሶቅራጥስ ደግሞ ሰው ነው ስለዚህም ሶቅራጥስ ሰው ስለሆነ ማሰብ ይችላል ማለት ነው ይኸ ደግሞ ሁልጊዜ አይሠራም። ምክንያቱም ሰው ሁሉ ማሰብ ይችላል ማለት ሞኝነት ነውና» ይለናል። በአጭሩ የእያንዳንዱ ሰው ሐሳብ ትክክለኛ ነው ማለት እስካልተቻለ ድረስ ስለ አንድ ነገር ማስብ ብቻ አንድን ነገር እውነት አያደርገውም ማለቱ ነው።
ጥበብ ከጲላጦስ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot