Code 1
የፍቅር አልሜ የሂወት ምዕራፎ
አንተን ያለምኩ ለት መስመሬን አልፎ
ያኔ ይጀምራል መራራው ሂወቴ
ገና ባፍላ እድሜዬ በጨቅላ አንደበቴ
ያኔ በልጅነት በለጋው እድሜዬ
በማላውቀው ስሜት ያነገስኩህ ስዬ
ደሰ የሚል ስቃዬ እልፍ አላፍ ብሶቴ
ገና አይንህን ሳየው ጠፍቶኝ እኔነቴ
አንዳች ስሜት መቶ ውስጤን ተቆጣጥሮ
መናገር ስሞክር ቃሌ ተሰባብሮ
ይሰማኛል ድምፄ ትርጉም አልባ ሁኖ
የውስጥ ስሜቴ ከሀሳቤ በኖ
እንጂማ ባወጋህ ድፍረቱን ታድዬ
ውስጤን አዳምጬ አንደበቴን ሰዬ
እኋው ልማልልህ ልጅነቴን ይንሳኝ ብዬ ተገዝቼ
አንተን ይንሳኝ ብዬ አለሜን አጥቼ
እኔ እንደምወድህ እራሰህን አቶድም
የኔን ፍቅር ብታይ ማፍቀርን አታውቅም
ድንገት ብታይማ ለማየት አድሎህ
በዕንባ ዘለላዬ ብዕሬን አቅልሜ
በዜማ ተውቦ የውሰጥ ህመሜ
በልቤ ያረፉት ረቂቃ ቃሎቼ
እልፍ አላፍ ግጥሞቼ
ይናገሩ ነበር ካንደበቴ በላይ የውስጤን አጉልተው
ቃል የሌለው ፍቅር መሆኑን ተረድተው
እንጂማ ባወጋህ ድፍረቱን ታድዬ
ውስጤን አዳምጬ አንደበቴን ስዬ
እኋው ልማልልህ ልጅነቴን ይንሳኝ ብዬ ተገዝቼ
አንተን ይንሳኝ ብዬ አለሜን አጥቼ
እኔ እንደምወድህ እራስህን አቶድም
የኔን ፍቅር ብታይ ማፍቀርን አታውቅም
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አንዳንዴ ሲብሰኝ እምባዬ ሲቀድመኝ😥
አፌ ተቆላልፎ የውስጤን ሸሽጎ
በይመጣል ናፍቆት ነገን ተስፋ አድርጎ
በመጠበቅ ደዌ በማይልቅ ለቅሷ
አንተነትህ ነግሷ ከልቤ ምሷሷ
ፊት ለፊት ላወጋህ ያጣሁትን ድፍረት
ብዕሬን አውግቼው ውስጤ ያለውን እውነት
ልሂድ ወይስ ይምጣ እያልኩ ሳንገራግር
ስሜቴን ሸሽጌ በይሉንታ አጥር
በመሀል እረፍዶ
ጆሮዬ ቢያሰማኝ የሰረግህን መርዶ
ሊያገባ ነው ቢሉኝ ከኔ ሌላ ወዶ
ዳግም ላይመለስ
ጎጆውን ሊቀልሰ
ሊሄድ ነው ሊያገባ አንቺን ይሉንታ አጥሮሽ
ሸሽገሽ ያኖርሺው እውነተኝ ፍቅርሽ
እንዲያ ብለው ሲሉኝ
ያኔ እንኩዋን ሳያገርመኝ
ከገደበኝ አጥር የይሉንታ መንደር
የዕድሜ እኩሌታዬን የጠበኩት ፍቅር
ከደስታው ታድሜ
ከሰርጉ ሙዚቃው
እሰክሰታና ፌሽታው
የልጅነት ህልሜን ዳርኩት እያለቀስኩ
ያብርሀም የሳራ ትዳር ይሁን እያልኩ
✍ Helen
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot
የፍቅር አልሜ የሂወት ምዕራፎ
አንተን ያለምኩ ለት መስመሬን አልፎ
ያኔ ይጀምራል መራራው ሂወቴ
ገና ባፍላ እድሜዬ በጨቅላ አንደበቴ
ያኔ በልጅነት በለጋው እድሜዬ
በማላውቀው ስሜት ያነገስኩህ ስዬ
ደሰ የሚል ስቃዬ እልፍ አላፍ ብሶቴ
ገና አይንህን ሳየው ጠፍቶኝ እኔነቴ
አንዳች ስሜት መቶ ውስጤን ተቆጣጥሮ
መናገር ስሞክር ቃሌ ተሰባብሮ
ይሰማኛል ድምፄ ትርጉም አልባ ሁኖ
የውስጥ ስሜቴ ከሀሳቤ በኖ
እንጂማ ባወጋህ ድፍረቱን ታድዬ
ውስጤን አዳምጬ አንደበቴን ሰዬ
እኋው ልማልልህ ልጅነቴን ይንሳኝ ብዬ ተገዝቼ
አንተን ይንሳኝ ብዬ አለሜን አጥቼ
እኔ እንደምወድህ እራሰህን አቶድም
የኔን ፍቅር ብታይ ማፍቀርን አታውቅም
ድንገት ብታይማ ለማየት አድሎህ
በዕንባ ዘለላዬ ብዕሬን አቅልሜ
በዜማ ተውቦ የውሰጥ ህመሜ
በልቤ ያረፉት ረቂቃ ቃሎቼ
እልፍ አላፍ ግጥሞቼ
ይናገሩ ነበር ካንደበቴ በላይ የውስጤን አጉልተው
ቃል የሌለው ፍቅር መሆኑን ተረድተው
እንጂማ ባወጋህ ድፍረቱን ታድዬ
ውስጤን አዳምጬ አንደበቴን ስዬ
እኋው ልማልልህ ልጅነቴን ይንሳኝ ብዬ ተገዝቼ
አንተን ይንሳኝ ብዬ አለሜን አጥቼ
እኔ እንደምወድህ እራስህን አቶድም
የኔን ፍቅር ብታይ ማፍቀርን አታውቅም
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
አንዳንዴ ሲብሰኝ እምባዬ ሲቀድመኝ😥
አፌ ተቆላልፎ የውስጤን ሸሽጎ
በይመጣል ናፍቆት ነገን ተስፋ አድርጎ
በመጠበቅ ደዌ በማይልቅ ለቅሷ
አንተነትህ ነግሷ ከልቤ ምሷሷ
ፊት ለፊት ላወጋህ ያጣሁትን ድፍረት
ብዕሬን አውግቼው ውስጤ ያለውን እውነት
ልሂድ ወይስ ይምጣ እያልኩ ሳንገራግር
ስሜቴን ሸሽጌ በይሉንታ አጥር
በመሀል እረፍዶ
ጆሮዬ ቢያሰማኝ የሰረግህን መርዶ
ሊያገባ ነው ቢሉኝ ከኔ ሌላ ወዶ
ዳግም ላይመለስ
ጎጆውን ሊቀልሰ
ሊሄድ ነው ሊያገባ አንቺን ይሉንታ አጥሮሽ
ሸሽገሽ ያኖርሺው እውነተኝ ፍቅርሽ
እንዲያ ብለው ሲሉኝ
ያኔ እንኩዋን ሳያገርመኝ
ከገደበኝ አጥር የይሉንታ መንደር
የዕድሜ እኩሌታዬን የጠበኩት ፍቅር
ከደስታው ታድሜ
ከሰርጉ ሙዚቃው
እሰክሰታና ፌሽታው
የልጅነት ህልሜን ዳርኩት እያለቀስኩ
ያብርሀም የሳራ ትዳር ይሁን እያልኩ
✍ Helen
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot