#Code_3
#ሳትስሚኝ በፊት
...አንዴ ስሚኝ
የምነግርሽ አለኝ
የምታዳምጪኝ
አዎ
ስለኖርኩት የልቤ ሀቅ
ስለሳቅኩት የጥርሴ ሳቅ
...ደሞ
ሳይቀያየሙ ስለመታረቅ
እየተያዩ ስለመናፈቅ
ስለመነፋፈቅ
ፍቅርን ስለመኖር
ፍቅርን ስለማኖር
...ብቻ በጣም ብዙ ነገር
ልነግርሽ እያሰብኩኝ ነበር
...ግና
ከዝርዝሩ በፊት
ከሁሉም ከሁሉም
አለኝ ደግ ምርቃት
ለኔም ሆነ ላንቺም
በይ ተቀበይ
የወዳጅ ምርቃት
ከቶ አይናቅም
...እስኪ አሜን በይ
...እስኪ ይሁን በይ
ልመርቅ ተቀበይ
ከጠላቴ ልታረቅ
ጠላትሽም ይናቅ
አሜን!
ክፉዬ ካንቺ ይጥፋ
ክፉሽ ከኔ ይራቅ
አሜን!
ቀኔ ባንቺ ይፍካ
ቀንሽ በኔ ይድመቅ
አሜን!
ከኔ ተደበቂ
ባንቺ ውስጥ ልደበቅ
አሜን!
ከኔ ይሁን እንባሽ
ካንቺ ይሁን ሳቄ
አሜን!
አወጪኝ "ከዚ አለም"
ላውጣሽ ነጥቄ
አሜን አሜን አሜን!
ሁሉም ይሁን ያፌን
...ታዲያ
በስሜ የማልኩት
በስምሽ ያስማለኝ
ሁሉንም ያስባለ
"እነግርሻለሁ"
ልኩት ሁሉ
ምርቃቴ ውስጥ አለ
አዎ...አሜን በይ
አዎ...ይሁን በይ
አሁን ግን
ላንድ አፍታ አንዴ
...ሁሉንም ተይ
ዕድሜሽን ሳልቀማው
ዕድሜዬን ሳትቀሚኝ
ለማንም ሳላማሽ
ለማንም ሳታሚኝ
ከበሽታሽ ዕድን ዘንድ
እንድታስታምሚኝ
ሁሉንም ተይና
አሁን በይ
...ጥግ ድረስ ሳሚኝ!
✍ሳሚ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot
#ሳትስሚኝ በፊት
...አንዴ ስሚኝ
የምነግርሽ አለኝ
የምታዳምጪኝ
አዎ
ስለኖርኩት የልቤ ሀቅ
ስለሳቅኩት የጥርሴ ሳቅ
...ደሞ
ሳይቀያየሙ ስለመታረቅ
እየተያዩ ስለመናፈቅ
ስለመነፋፈቅ
ፍቅርን ስለመኖር
ፍቅርን ስለማኖር
...ብቻ በጣም ብዙ ነገር
ልነግርሽ እያሰብኩኝ ነበር
...ግና
ከዝርዝሩ በፊት
ከሁሉም ከሁሉም
አለኝ ደግ ምርቃት
ለኔም ሆነ ላንቺም
በይ ተቀበይ
የወዳጅ ምርቃት
ከቶ አይናቅም
...እስኪ አሜን በይ
...እስኪ ይሁን በይ
ልመርቅ ተቀበይ
ከጠላቴ ልታረቅ
ጠላትሽም ይናቅ
አሜን!
ክፉዬ ካንቺ ይጥፋ
ክፉሽ ከኔ ይራቅ
አሜን!
ቀኔ ባንቺ ይፍካ
ቀንሽ በኔ ይድመቅ
አሜን!
ከኔ ተደበቂ
ባንቺ ውስጥ ልደበቅ
አሜን!
ከኔ ይሁን እንባሽ
ካንቺ ይሁን ሳቄ
አሜን!
አወጪኝ "ከዚ አለም"
ላውጣሽ ነጥቄ
አሜን አሜን አሜን!
ሁሉም ይሁን ያፌን
...ታዲያ
በስሜ የማልኩት
በስምሽ ያስማለኝ
ሁሉንም ያስባለ
"እነግርሻለሁ"
ልኩት ሁሉ
ምርቃቴ ውስጥ አለ
አዎ...አሜን በይ
አዎ...ይሁን በይ
አሁን ግን
ላንድ አፍታ አንዴ
...ሁሉንም ተይ
ዕድሜሽን ሳልቀማው
ዕድሜዬን ሳትቀሚኝ
ለማንም ሳላማሽ
ለማንም ሳታሚኝ
ከበሽታሽ ዕድን ዘንድ
እንድታስታምሚኝ
ሁሉንም ተይና
አሁን በይ
...ጥግ ድረስ ሳሚኝ!
✍ሳሚ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot