Forward from: ᴘᴀᴛʜ ᴏꜰ ʜᴇᴀᴠᴇɴ(ᴊᴇɴɴᴀʜ)
#ቀን ሲጥል
#ክፍል 2
በላይ ኤቤጊያ ብሎ ሲጣራ በድንጋጤ ብዛት ጭልፊት እንዳየች አይጥ ዘልዬ ወደውስጥ ገብቼ አልጋዬ ውስጥ ተደበቅኩ። በላይ ማለት በጣም እሚያናደኝ ልጅ ነው ኤቤግያን እንደምወዳት አውቆ ሁሌም ይፈታተነኛል ሞኝ የሆነ ልጅ ነው ፍቅር የማይገባው ብዙ ግዜ አንስማማም።
ሁሉም የዶርም ልጆች ሁኔታዬን እያዩ ይበልጥ ተሳሳቁብኝ ተናድጄ ተነሳውና በላይን ምን መሆንህ ነው ምትጠራት አልኩት መልስ አልሰጠኝም ዝምብሎ ይገለፍጣል ድሮም እንዲው ነው ከማግጠጥ ሌላ ምንም አያቅም ጅል!!! ወደ አልጋዬ ተመለስኩና በመስታወቱ በኩል ሆኜ ስታልፍ አየኃት አዬ እዳ ምን ቀን ነው ያየኃት ኤቤጊያ ካለፈች በኃላ ሁሉም ወደ ውስጥ ገቡ ኪያር ና ምሳ እንብላ አለኝ ወደ አልጋዬ አጮልቆ እያየ አልበላም አልኩት እሺ ብሎኝ ሄደ ኪያ ደስ እሚለኝ ለዚ ነው መጨቃጨቅ መጋተት ምናምን አይመቸውም እኔም አልወድም አልፈልግም ካልኩ አልኩ ነው ተመልሼ እንቅልፌን ለጠጥኩ።
10፡00 ሰአት አከባቢ ከእንቅልፌ ነቃው ዶርም ማንም የለም ሁሉም ክላስ ሄደዋል ከአልጋዬ ተነሳውና ወደሎከሬ ሄድኩ ልክ ሎከሩን ስከፍተው ሁለት ትንንሽ አይጦች ጫማዬን እያጣጣሙ ሲግጡት አየው ልክ እኔን ሲያዩ ተፈትልከው በእግሬ ስር እየተሽሎከሎኩ ፈረጠጡ እማማዬ .... ብዬ ለጉድ ጮህኩ ሲያስጠሉ ቀፋፊዎች ነብሴ መለስ ስትል ዝርክርክ ካለው ልብሶቼ ውስጥ እምለብሰውን ልብስ መፈለግ ጀመርኩ።
ሁሉም ልብስ ከታጠበ በጣም ቆይቷል በግ በግ ይሸታል ደና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ አደል ያለችው አያቴ ከበክት ውስጥ ትንሽ የበከተውን ልብስ መፈለግ ጀመርኩ አንድ ድሮ ሳውቀው ነጭ የነበረ አሁን ግን መንችኮ ቡኒ የሆነ ሰፊ ሸርት አገኘው ለበስኩት ከታችም ቆሻሻ የቃመ ሰፊ ሰማያዊ ጅንስ አርጌ ቅድም አይጦቹ የገጠቡትን ጫማ ያለካልሲ አድርጌ ከዶርም ወጣው ወዴት እንደምሄድ አላውቅም እግሬ ወደመራኝ ብቻ ከዚ ግቢ ውጪ ብቻ ይሁን ድንዝዝ ብዬ ከግቢያችን ወጣው ናዝሬት የለመደባትን ፀሃይ በአናት በአናቴ ትለቅብኛለች።
#የግቢያችንን በር አልፌ ፊትለፊት ወዳለው ሱቆች ሄድኩ ባለሱቁ ደስታ ሁሌም ያቀኛል ሳልጠይቀው አንድ ፓኮ ሲጋራ እጄ ላይ አስቀመጠልኝ ብሩን ከኪሰ በርብሬ አውጥቼ ከፍዬው መንገዴን ቀጠልኩ የግቢያችን ተማሪዎች ታክሲ አጥተው መደዳውን በር አከባቢ ተደርድራው ይጠብቃሉ አንድ ኮሳሳ ታክሲ ስትመጣ ተሯሩጠው እየተጋፉ ይገባሉ።
በእግር መንገዴን ወደ መብራት ሃይል አደረኩ ደስታ ከሰጠኝ ፓኮ ሲጋራ ፈልቅቄ አንዷን አውጥቼ አፌ ላይ ሰክቼ ኪሴ ውስጥ ክብሪት ፍለጋ ማሰንኩ የቅድሙ ሱሪ ውስጥ እንደረሳሁት ትዝ አለኝ ተበሳጨው አከባቢዬ ላይ የእሳት ምንጭ የሚገኝበት መንስኤ ማሰስ ጀመርኩ ከርቀት አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ልጅ በተሰበረ ምድጃ እሳት ስታቀጣጥል አየው እየሮጥኩ ወደሷ ሄድኩ እሙዬ እሳት ልጫር አልኳት እሺ አለችኝ ሲጋራውን ከአፌ ሳልነቅል አጎንብሼ አፌ ላይ እንዳለ የእንጨቱን ጭስ እየታጠንኩ ለኮስኩት ልጅቷ ገርሟት ታየኛለች እኔ ግን መንገዴን ቀጠልኩ ብቻዬን በሃሳብ አለም እየዋለልኩ እግሬ ወደሚወስደኝ ቀጠልኩ።
ኤቤጊያን እንዴት እንደዚ እስከምሆን ድረስ ላፈቅራት ቻልኩ ሁሌም ስለሷ ሳላስብ አይነጋም አይመሽም እሚገርመው ግን እሷ እኔ አይደለም እንደምወዳት ቀርቶ ማን እንደሆንኩ እንኳን አታውቅም ኤቤግያ የአዲስ አበባ ልጅ ናት እኔም የዛሬን አያድርገውና የፒያሳ ልጅ ነበርኩ ነቄ ሁሉን ያየው ግን ምን ያደርጋል ፍቅር ሲይዝ ሳያስጠነቅቅ ነው ልክፍት ነው የኔማ ሳያት ሁላ እምገባበት ነው ሚጠፋኝ።
#እንዲ በሃሳብ እየተብሰለሰልኩ መብራትሃይል አከባቢ ደረስኩ ግማሹ ፓኮ ሲጋራ አልቋል ሆዴን በምግብ ሳይሆን በጭስ የሞላሁት መሰለኝ ከነጋ አልበላሁም 11፡30 ሆኗል ሆዴ ያኮረፈ ይመስል ያጉረመርማል አስፓልቱ ዳር ካሉት የተቀቀለ ድንች ሻጮች ጋር ሄድኩና ሁለት እንቁላል በዳባና ሚጥሚጣ እዛው አጠገባቸው አስፓልት ዳር ሆኜ በላውና ተነስቼ መንከራተቴን ቀጠልኩ ድንገት የሞባይል ቤት አየውና አንድ ሃሳብ መጣልኝ
ለአቤጊያ ብቻ እምደውልበት አዲስ ሲም ማውጣት! ወደሱቁ ገብቼ አንድ አዲስ ሲም ገዝቼ ወጣው ከዛ ወደለመድኩት ባር ሄድኩ ድራፍቴን ስጋት ስጋት ስጋት አመሸው ማታ ላይ ወደግቢ ስመለስ አዳልጦኝ አንድ ቱቦ ውስጥ ወደቅኩ በቆሻሻ ውሃ ጨቅይቷል ኤጭ የራሱ ጉዳይ! እዚው አድራለው ቀን የገዛሁትን ሲጋራ በጣም የሚሸተው ውሃ ውስጥ ካለው ኪሴ አውጥቼ ያልበሰበሱትን አውጥቼ ባር ውስጥ በተቀበልኩት ላይተር ለኩሼ ሁሉንም አፌ ውስጥ ሞጀርኳቸው ....
ክፍል ሶስት እንዲቀጥል 👍👍
#share and join us
@ethiokeld3