#ሶስተኛው የዓለም ጦርነት
ክፍል_አንድ
ከምኔው እንደ መሸ ስራዋን ገታ አድርጋ ስታስበው ተዓምር እንደሆነባት ለእራሷ መልሳ አጫወተችው- በእነ አቶ መኩሪያ ቤት ተከራይታ የምትቀመጠው ፍቅር።
"አቤቱ ፀሃይን በምስራቅ አውጥተህ በምዕራብ የምታጠልቅ አምላክ በሁሉም ሐይማኖቶች ስምክ ይባረክ..."ቧንቧው አጠገብ ቆማ የሃያ ሶስት ዓመቷ ወጣት በሆዷ አይኖቿን ወደ ሰማይ ልካ ታመሰግነዋለች።
ከሚወዳቸው ተማሪዎቹ ለሁለት ቀናት የተለያቸው የፍቅር ጎሮቤት የሆነው መምህር አየለ ስልክ እየነካካ ወደ ቧንቧው ሲመጣ ያላስተዋለችው መላዕክትን አስቶ የሚጥለውን ጀርባዋን ሰጥታው ስለቆመች እንጂ "..አንዴ መንገድ.."ሲላት በወንዳወንድ ድምፅ አትደነግጥም ነበር።
ሃብትን ከቁንጅና የያዘው ተቀጥራ የምትሰራበት ድርጅት ባለቤት የሆነው ዕዝራ ያላስደነገጣት፤ የቢሻው ሰውነት ያላስደመማት ቁንጅናን ከፈጣሪ የፈጠራ ክፍል ገዝታው የወረደች የምትመስለው ፍቅር እንደ በድን ደርቃ ቀረች።
ሰይጣን ንቀትን ከማን ተማረ ቢባሉ እና ከ አየለ ነው ቢሉ ምንም ስህተት የለውም።
አይኖቹን ከስልኩ ሳይነቅላቸው ሲቀር ሃሳቡን ለመሳብ ብላ "ወይኔ እግሬን"ብትል በአንድ አይኑ አጮልቆ ከገላመጣት በኋላ ምንም ሳይናገራት ቧንቧውን ዘግቶ በአሮንጓዴ ባልዲ የሞላውን ውሃ በቀኝ እጁ እንዳንጠለጠለው ወደ ቤቱ ገባ።
ፍቅር አበደች። አበደች ከምለው ይልቅ ሰይጣን ሆነች ይቀላል። ወደ መምህር አየለ ቤት እየተጣደፈች ሄደች...
አየለ እየተመለከተ የነበረውን የአለቃውን ትዕዛዝ በኢሜል ተቀብሎ እቅድ እያወጣ ሳለ የቤቱ በር ኃይል በተሞላበት ምት ተንኳኳ።
"... እንደሆነ የዚህን ወር የቤት ክራይ ከፍያለው፤ታድያ አቶ መኩሪያ ምን ፈለጉ?..."ጠየቀ እራሱን።
አሁንም ተንኳኳ። በመጀመሪያው ምንም አይነት መልስ ስላልሰጠ "ማነው?"አለ በተረጋጋ መንፈስ።
አሁን በዝግታ ተንኳኳ። እሱን እና እሱን ብቻ በምታስተኛው ትንሿ መሬት ላይ ከተነጠፈችው ፍራሹ ያን ፈርጣማ ሰውነቱን ተሸክሞ ብድግ አለ።
ሰፊ ከብቶች የሚሰማሩበት ከመሰለው ፊቱ እንደ ጥቅጥቅ የአማዞን ደን የበቀለው ፂሙ ላይ የመኮሳተር ስሜት ሲያሳይ፥ የጠዋት ኮከብ የመሰሉት ከዓይኖቹ በላይ ያሉት በፀጉር የተሸለሙት ቅንድቦቹ ግርማ ሞገስ ይሰጡታል።
እግዚአብሔር የእጁን ጣቶች አለስልሶ የፈጠረው እንዲፅፍበት ብቻ እንዳልሆነ ፍቅር የተረዳችው የተከራየበትን የእነ አቶ መኩሪያን ቤት በር በትህትና ሲከፍተው ነው።
ከአናቱ በላይ ያለው ጠቋቁር ፀጉሮች "...ተጨቆን ድረሱልን..."እንደሚሉ ለመረዳት ሰው መሆን በቂ ነው።
ከአናቱ ዝቅ ብሎ የሚገኙት መንቲያ ጆሮቹም ሲቆሙ መመልከት ያስፈራል።
የለበሰው ቁምጣ የእግሮቹን ማማር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
የለበሰው ሲሊፐር ግን መምህር እንደሆነ አይናገርም።"...አቤት..."አላት በሩን በቀኝ እጁ እንደያዘ ኮስተር ብሎ።
"...እእእ እንትን ፈልጌ ነበር..."ሳታውቀው ተርበተበተች። ፍርሃትን በስም እንጂ በአካል አታውቀውም፤ዛሬ ገና ተዋወቀችው።
በሆዱ "እንትንሽ እንትን ይሁንና..."
"እሺ ምን?"አላት
"...እንትን...ባልዲ ፈልጌ ነበር..."ፊቷ ይንቀጠቀጣል።
በቁም ያለ በድን ማንን ታውቃለክ ተብሎ አየለ በዚያ ጊዜ ቢጠየቅ ፍቅርን ነው ማለቱ እንደ ማይቀር የተረዳችው ልክ እሱ ባልዲው ሊሰጣት ሲግባ ከፊት ለፊቷ በተሰቀለው መስታወት ስትመለከተው ነው
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመድዎ #share @Qdist
Join&share 👉
@Qdist
@Qdist
@Qdist
For any comment&question ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👉 @e_t_l_bot