#ቀን_ሲጥል
ኪያር በእህቴ በኩል መጣና ቆይ ላግዝሽ ሲላት ቦታውን ለሱ ለቀቀችለት እና ወደ እናታችን ጋር ሄደ በስንት ትግል መኪናው ጋር ደረስን ላብ በላብ ሆኛለው አባቴ ቀድሞ በሩን ከፍቶልን ገባን ሰምሃል በጣም ደብሯታል በቃ አትጥፋ እሺ ቤት መጥቼ እጠይቅሃለው እግዜር ይማርህ አለችኝ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም በጣም ነው ማመሰግነው ሰሙ አንቺም አትጥፊ እደውልልሻለው ስልክሽን እህቴ ጋር ተዪልኝ እና ሂጂ አልኳት።
ሳቅ እያለች እሺ ብላ ስልኳን ለእህቴ ነግራት ልትሄድ ስትል አባቴ ጠራት ድንግጥ ብላ አቤት ጋሼ አለችው አባቴ እየሳቀ ወደሷ ተጠጋና በጣም ነው እማማሰግንሽ ልጄን ስላዳንሽልኝ ውለታሽን በምን እንደምከፍል ወላውቅም ብቻ... እያለ ወደኪሱ ገብቶ ብር ሊያወጣ ሲል አረ በእግዜር ጋሼ እኔ ምንም አላደረኩም ማንም ሰው እሚያደርገውን ነገር ነው ያደረኩት ምንም ብር አያስፈልግም ጋሼ አልቀበሎትም በእውነት የሰራሁትን ስራ በብር አይቀይሩብኝ አያስፈልግም ብላ እጁን ይዛ አስተወችው በግድ ሊሰጣት ሲል አይሆንም ብላ እየሮጠች ሄደች።
ሁላችን አረ ተቀበይው አልናት እየተሳሳቅን እሷም እየሳቀች አይሆንም እቤት መጥቼ እጠይቅሃለው በቃ ቻው ብላኝ ሄደች አባቴ እየሳቀ ወደመኪናው ገባ እህቴም ከኔና ከኪያር ጋር ከኃላ ተቀመጥን እናቴ ከፊት ገባች ኪያር እቤት አድርሶኝ በዛውም ቤተሰቦቹን አዲስ አበባ ጠይቆ ሊመለስ አስቧል።
መንገዳችንን አቅንተን ከ1፡30 ሰአት ጉዞ በኃላ አዲስ አበባ ቦሌ አከባቢ ደረስን ሰፈራችን ቤት ገባን ይዘውኝ ወጥተው ወደ ሳሎን በኪያር እና በእህቴ እገዛ ገባው ደክሞኝ ስለነበር ሶፋው ላይ ተኛው።
ኪያር እራት ከበላ በኃላ ስለመሸ በግድ ካላደርክ አልኩት እሱም ያው እየደበረው እሺ አለኝ። እንደለመድኩት በእህቴና በእሱ እገዛ ሁለተኛው ፎቅ መኝታ ክፍሌ ላይ በመከራ ይዘውኝ ወጡ እናቴ ከኃላ ተከትላን ገባች አልጋው ላይ ከተኛው በኃላ ምን ላምጣላችው አለችን ምንም እምንፈልገው ነገር አልነበረም እህቴና እናቴ ወጡ። ልክ እነሱ እንደወጡ ኪያር ወደኔ እያፈጠጠ እሺ... የቅባት ልጅ እንደዚ ሲያዩሽ የሸራ ቤት ውስጥ እምትኖር ቦርኮ ነበር ምትመስለው ለማያውቅች እእእ ለካ እንዲ የተጃር ልጅ ነሽ አለኝ እየሳቀ ክፍሉን በአይኖቹ እየቃኝ ሆዴን ቢያመኝም ከት ብዬ ሳቅኩ ባክህ ሃብት ምን ያረጋል ጥቅም የለውም እፕልኩት እሱም እየሳቅ ስላለህ ነዋ ምንም እማይነስልህ አለኝ።
ይልቁንስ እሱን ተወውና ኤቤጊያን አናግርልኝ በናትህ ያው እኔ ሲሻለኝ እመጣለው አልኩት ወሬ ለማስቀየስ ይመስል ኪያር በግርምት እያየኝ ትንሽ አታፍርም እንዴ ቆይ አንተ ሌላው ቢቀር እንኳን ለራስህ ክብር ይኑርህ እንጂ እንደዛ ውሻ አድርጋህ ሄዳ አሁንም ወዳታለው ልትለኝ ባልሆነ እፈር ጌታ...ትን እፈር አንተ የምር አመት ከምናምን ከሰውነት ተራ ወጥተ መርፌ እስክታክል ድረስ ወደሃት ምን ፈየደልህ እእእ ሰድባህ አይደል እንዴ የሄደችው ያውም እንደዚ ሆነህ እያየችህ ለመሆኑ የሰደበችህን ስድብ ራሱ ልብ ብለኀዋል እኔ ላንተ በጣም እየረሰናኝ ነበር የምር ናኦድ እርሳት በቃ አትበጅህም ተዋት አለኝ ተበሳጨው እንዴት ነው ምረሳር እንዴት ነው እምተዋት ይሄን ሁሉ ግዜ ያቃጠልኩት ላላገኛት ነው እንዴ ... አልረሳትም መሄም አልረሳትም መቼም
ደነፋሁበት ወይ ናዲ እምልህን ስማኝ አተን ሌላ ሴት ጥበስ በቃ እሷን እርሳት እኔ አጣብስሃለው ከፈለክ ሌላ ሴት አንተ ብቻ እሺ በል አለኝ እምቢ አልኩት ኪያር ብርድልብሱን ጎትቶት አኩርፎ ተኛ እኔም እያመመኝ ስለነበር ተኛው።
ሲነጋ ኪያር ወደቤተሰቦቹጋ ሊሄድ በጥዋት ተነሳ ቤተሰቦቼም በስም ስለሚያውቁት አመስግነው ላኩት እህቴ ውጪ ድረስ ሸኝታው መጣች ስትመለስ እየሳቀች ነበር ምነው እላታልው እየተሽኮረመመች ምንም ብላኝ ወደክፍሏ ሄደች። እኔም ቀን ከቀን በቤተሰቦቼ እገዛ ራሴን ማስታመም መጠገን ጀመርኩ ቀናት እያለፉ በሳምንት ተተኩ አራት ወንድማማች ሳምንቶችም በአንድነት ተባብረው ወርን አስቆጠሩ
ይቀጥላል ....
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot