#የመገፋት ህመም የማጣትን ፍቺ
ልንገርሽ እንጂ እኔ የት አውቀሽው አንቺ
ብዙ ነገ እየሳልኩ አብሬ ካንቺ'ጋ
ሳስብሽ አመሸሁ እያለምኩሽ ነጋ
ሀሳቤን ሰርቀሽው ቀኔ አላማረበት
ቀልቤን ሰውረሽው አዋዋል ጠፋበት
ከእኔ'ጋ ነሽ እያልኩ አብረሽኝ ከጎኔ
አንቺ ሩቅ ሄደሻል እዛው ቀረሁ እኔ
የቀረበሽ ልቤ አንቺን በወደደ
የማያውቀው ነፍሴ በእሳትሽ ነደደ
መላ አካሌ አፍቅሮሽ እኔን ጥሎ አበደ
የኔ ያልኩት ሁሉ ትቶኝ ተሰደደ
እፋረድሻለሁ በይ ካሽኝ እያልኩኝ
ለብቻየ ስቀር ብዙ እንዳልነበርኩኝ
ለማን ዳኛ ልክሰስ ማንስ ይሰማኛል
ጉዳቴን ያሰበስ ምንድን ይክሰኛል
ጉዳዬን የሰማ ያ ሁሉ ዳኛ ሰው
ክሴን አቃለለ ብሶቴን መለሰው
እንግዲህ ምን ላድርግ...
ፍትህ ንብረት አይደል አልገዛ አልዋሰው
የሰማኝ በሙሉ የነገርኩት ዳኛ
እሷን ነፃ አረጋት እኔን ጥፋተኛ
ከእንግዲህ ለማንም አልከስም በቅቶኛል
እስካሁን የሰማኝ አይሆንም ብሎኛል
አንቺ ጉልበተኛ አንቺ ባለጊዜ
እኔ ሟች ደካማ የዋጠኝ ትካዜ
አንቺን ማን ተሟግቶ ችሎ ያሸንፍሻል
የቀረበሽ ሁሉ ላንቺ ያዳላልሻል
ቁመናሽ እሳት ነው አይን ጥርስሽ ገመድ
ውበትሽ አሳሳች አሳሳቅሽ ወጥመድ
ማለፍ ቢሳናቸው ይሄንን ፈተና
እኔን 'በዳይ' ማለት ቀለላቸውና
እሷን ተበዳይ ሰው እኔን ወንጀለኛ
ብለው ፈረዱብኝ ከአንድም ሶስት ዳኛ
አምርሮ ቢያነባ እንባዬ ቢፈስም
በያገኘው ችሎት እልፍ ጊዜ ቢከስም
የፍርድን ጥም ሽቶ ከጫፍ ጫፍ ቢያስስም
ገሳጭ ሰው ነው እንጂ አይዞህ ባይ አይደርስም
በቃኝ አልካሰስ ይቅርብኝ ልጎዳ ልተወው ግዴለም
ብቻ አውቄዋለሁ በሰዎች ደጅ እንጂ ፍትህ በአገር የለም
አትፍሰስ ይበቃል ከእንግዲህ እንባዬ
ጩኸቴ አላዋጣም ይርታት ዝምታዬ
እንግዲህ ገብቶኛል...
ላገኘሁት ሰሚ አልከስ አልዘልፍሽም
በየአደባባዩ ስምሽን አልጠራሽም
በየችሎቱ በር ነይ ግቢ አልልሽም...
ስምሽን ባጠፋ ብሰድብሽም እንኳን አትደናገሪ
ጩኸቴ ምንም ነው ዝም ስል ግን ፍሪ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot
ልንገርሽ እንጂ እኔ የት አውቀሽው አንቺ
ብዙ ነገ እየሳልኩ አብሬ ካንቺ'ጋ
ሳስብሽ አመሸሁ እያለምኩሽ ነጋ
ሀሳቤን ሰርቀሽው ቀኔ አላማረበት
ቀልቤን ሰውረሽው አዋዋል ጠፋበት
ከእኔ'ጋ ነሽ እያልኩ አብረሽኝ ከጎኔ
አንቺ ሩቅ ሄደሻል እዛው ቀረሁ እኔ
የቀረበሽ ልቤ አንቺን በወደደ
የማያውቀው ነፍሴ በእሳትሽ ነደደ
መላ አካሌ አፍቅሮሽ እኔን ጥሎ አበደ
የኔ ያልኩት ሁሉ ትቶኝ ተሰደደ
እፋረድሻለሁ በይ ካሽኝ እያልኩኝ
ለብቻየ ስቀር ብዙ እንዳልነበርኩኝ
ለማን ዳኛ ልክሰስ ማንስ ይሰማኛል
ጉዳቴን ያሰበስ ምንድን ይክሰኛል
ጉዳዬን የሰማ ያ ሁሉ ዳኛ ሰው
ክሴን አቃለለ ብሶቴን መለሰው
እንግዲህ ምን ላድርግ...
ፍትህ ንብረት አይደል አልገዛ አልዋሰው
የሰማኝ በሙሉ የነገርኩት ዳኛ
እሷን ነፃ አረጋት እኔን ጥፋተኛ
ከእንግዲህ ለማንም አልከስም በቅቶኛል
እስካሁን የሰማኝ አይሆንም ብሎኛል
አንቺ ጉልበተኛ አንቺ ባለጊዜ
እኔ ሟች ደካማ የዋጠኝ ትካዜ
አንቺን ማን ተሟግቶ ችሎ ያሸንፍሻል
የቀረበሽ ሁሉ ላንቺ ያዳላልሻል
ቁመናሽ እሳት ነው አይን ጥርስሽ ገመድ
ውበትሽ አሳሳች አሳሳቅሽ ወጥመድ
ማለፍ ቢሳናቸው ይሄንን ፈተና
እኔን 'በዳይ' ማለት ቀለላቸውና
እሷን ተበዳይ ሰው እኔን ወንጀለኛ
ብለው ፈረዱብኝ ከአንድም ሶስት ዳኛ
አምርሮ ቢያነባ እንባዬ ቢፈስም
በያገኘው ችሎት እልፍ ጊዜ ቢከስም
የፍርድን ጥም ሽቶ ከጫፍ ጫፍ ቢያስስም
ገሳጭ ሰው ነው እንጂ አይዞህ ባይ አይደርስም
በቃኝ አልካሰስ ይቅርብኝ ልጎዳ ልተወው ግዴለም
ብቻ አውቄዋለሁ በሰዎች ደጅ እንጂ ፍትህ በአገር የለም
አትፍሰስ ይበቃል ከእንግዲህ እንባዬ
ጩኸቴ አላዋጣም ይርታት ዝምታዬ
እንግዲህ ገብቶኛል...
ላገኘሁት ሰሚ አልከስ አልዘልፍሽም
በየአደባባዩ ስምሽን አልጠራሽም
በየችሎቱ በር ነይ ግቢ አልልሽም...
ስምሽን ባጠፋ ብሰድብሽም እንኳን አትደናገሪ
ጩኸቴ ምንም ነው ዝም ስል ግን ፍሪ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot