ሰዉ እምድላድር ላይ
አንጋጦ ወደ ላይ
ሲመራመር ውሎ
ሰማይን ከምድር ሊያስተሳስር ምሎ
አውጥቶ አውርዶ
በምስራች መርዶ
በመሰለው ሁሉ
ስምን የሚያወጣው መላክት ነው ሲሉ
ከት ብዬ ሳኩኝ ስለመጣራቸው
አንቺን እስካገኝሽ ውሸት ነው ብያቸው
ዮርዳኖስ ያሉሽን ሳለምድልሽ ገና
ቤት ለቤት ሊያ ነሽ ሲባል ሰማሁና
እስኪ ልፈራረድ ብሂሉን ብዬልሽ
ቀልቤን ጥዬ ገባው ልቤን አንግቤልሽ
አወይ የኔስ እዳ የኔው ሞኝነት
ታሪኬን ሳወጋ አመታት አልፎት
እንደ አዲስ ትዝታ ዛሬም ይሰማኛል
ሰላምታዬ ሳይቀር ዘንድሮም ወርሶኛል
በንባሽ የታጠቡ ያለፉት ቀኖቼ
ፅዱ ሆነው ቀርተው ቢሳሉ ካይኖቼ
ባየሁት ብሌን ውስጥ ሁሌ ነው ማያቸው
ህመሜን ሚሽሩት አይኖችሽ ናፍቋቸው
ኡኡታን ለሚያውቅ እህህንም እንዲያ
ፍቅርሽ ያባክናል ካበገነ ወዲያ
አለምን አምላክሽ ቢያረግልኝ ደብተር
ፅፌ ብጨርሰው አይወጣልኝ ነበር
ናፍቀሺኛል እሺ…ስምሽ ጋር ልመለስ
በጣም ተናፍቀሻል ሀሞቴ እንኳ ቢፈስ
ስላንቺ ማንሳቱን ይፍታህ ላሉኝ አባ ባላቆምም እኔ
በመሸልሽ ቁጥር ጭሴን ተከትዬ
አለሁኝ ለምትል አለሁልሽ ብዬ
ያንተ ነኝ ለምትል ያንቺ ነኝ እያልኩኝ
አንቺን እያሰብኩኝ
ተአምር እያለምኩኝ
ትመጫለሽ ብዬ እያበድኩኝ እኔ
የሆዴን በሆዴ እርዳታ ለምኔ
አምላክ እንኳ አልቻለም
ብዬ ስለፎከርኩ
ለእኔና አንቺ አለም
ምስክር ስላጣው
ይኼንን ፅፍያለው
ስላንቺ ለመፃፍ ብፈርጥ እንኳ እንደ እንቧይ
ቃላት አይበቃኝም ብባንን ሰማይ ላይ
ደመናን ሚቀዝፉ መላክቶች ጋር ካለው
ኼጄ ዝም አልልም እኔ ጠይቃለው
ለምን ካልጠፋ ስም በሞላ ባገሩ
የሷን በኔ ጣሉት አልገባኝም ውሉ
ለካ ስቼ ኖሯል መሳቄ የዛኔ
በማልቀስ ስተካው ገባኝ አሁን እኔ
ዬርዳኖስ ብለዋት በገላዬ ፈሳ
ህማሜን ተረድታ አክማው አድሳ
ታድጋኝ ከራሴ ለኔ ፈውስ ሆና
ማግኘቴን በማጣት እንዴት ብዬ ላውሳ
ደግሞም ሊያ ሆናኝ ስሟን ተደግፌ
ካምላኬ አርፌ በርሱ ተንሳፍፌ
ዘውድ ሆናኝ የአልማዝ አንፀባራቂዋ
በርትታ አበርትታኝ ጠንክራ በእምነትዋ
የኖህ ውሀ ቢሆን ጌታ ለኔ ያላት
ግራዬን እጉድላ በለጋ እድሜ ባያት
ነገር ባልገባኝ ለት
አጥሚት ባኘኩበት
ትዝታ ሆነና ታሪካችን ሁሉ
ብቻዬን ካየሺኝ እንደ እድልሽ ሆኖ
አንቺ ነሽ ሀሳቤ ጫጫታው ተከድኖ
ከእኔና አንቺ ውጪ ላሉት ቢሆን ሚስጥር
ባርስተ ሰላምታ ህመሜን ብናገር
መቼም እንዳትረሺ ፀሎቴ ፀሎትሽ ሆኖ እንደሚቀር
ይቅናሽ እንጂ አንቺን ኑሮሽ ይሳካና
አለኝ የምሰጥሽ የኑሮዬን ዳና
አሳትመሽ ሽጪው ወይ ካንቺው አስቀሪው
መድብል ሞልቶልሻል ልቤን ስታዝዪው
እሺ ታዲያ ጊዜ የተራረፋቹ
የኔን ስሜት የተካፈላቹ
በትዳር በፍቅር አብራቹ ላላቹ
በፍፁም አእምሮን ደርሶ እያመናቹ
ልባቹን አትግፉት ትሰቃያላቹ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot
አንጋጦ ወደ ላይ
ሲመራመር ውሎ
ሰማይን ከምድር ሊያስተሳስር ምሎ
አውጥቶ አውርዶ
በምስራች መርዶ
በመሰለው ሁሉ
ስምን የሚያወጣው መላክት ነው ሲሉ
ከት ብዬ ሳኩኝ ስለመጣራቸው
አንቺን እስካገኝሽ ውሸት ነው ብያቸው
ዮርዳኖስ ያሉሽን ሳለምድልሽ ገና
ቤት ለቤት ሊያ ነሽ ሲባል ሰማሁና
እስኪ ልፈራረድ ብሂሉን ብዬልሽ
ቀልቤን ጥዬ ገባው ልቤን አንግቤልሽ
አወይ የኔስ እዳ የኔው ሞኝነት
ታሪኬን ሳወጋ አመታት አልፎት
እንደ አዲስ ትዝታ ዛሬም ይሰማኛል
ሰላምታዬ ሳይቀር ዘንድሮም ወርሶኛል
በንባሽ የታጠቡ ያለፉት ቀኖቼ
ፅዱ ሆነው ቀርተው ቢሳሉ ካይኖቼ
ባየሁት ብሌን ውስጥ ሁሌ ነው ማያቸው
ህመሜን ሚሽሩት አይኖችሽ ናፍቋቸው
ኡኡታን ለሚያውቅ እህህንም እንዲያ
ፍቅርሽ ያባክናል ካበገነ ወዲያ
አለምን አምላክሽ ቢያረግልኝ ደብተር
ፅፌ ብጨርሰው አይወጣልኝ ነበር
ናፍቀሺኛል እሺ…ስምሽ ጋር ልመለስ
በጣም ተናፍቀሻል ሀሞቴ እንኳ ቢፈስ
ስላንቺ ማንሳቱን ይፍታህ ላሉኝ አባ ባላቆምም እኔ
በመሸልሽ ቁጥር ጭሴን ተከትዬ
አለሁኝ ለምትል አለሁልሽ ብዬ
ያንተ ነኝ ለምትል ያንቺ ነኝ እያልኩኝ
አንቺን እያሰብኩኝ
ተአምር እያለምኩኝ
ትመጫለሽ ብዬ እያበድኩኝ እኔ
የሆዴን በሆዴ እርዳታ ለምኔ
አምላክ እንኳ አልቻለም
ብዬ ስለፎከርኩ
ለእኔና አንቺ አለም
ምስክር ስላጣው
ይኼንን ፅፍያለው
ስላንቺ ለመፃፍ ብፈርጥ እንኳ እንደ እንቧይ
ቃላት አይበቃኝም ብባንን ሰማይ ላይ
ደመናን ሚቀዝፉ መላክቶች ጋር ካለው
ኼጄ ዝም አልልም እኔ ጠይቃለው
ለምን ካልጠፋ ስም በሞላ ባገሩ
የሷን በኔ ጣሉት አልገባኝም ውሉ
ለካ ስቼ ኖሯል መሳቄ የዛኔ
በማልቀስ ስተካው ገባኝ አሁን እኔ
ዬርዳኖስ ብለዋት በገላዬ ፈሳ
ህማሜን ተረድታ አክማው አድሳ
ታድጋኝ ከራሴ ለኔ ፈውስ ሆና
ማግኘቴን በማጣት እንዴት ብዬ ላውሳ
ደግሞም ሊያ ሆናኝ ስሟን ተደግፌ
ካምላኬ አርፌ በርሱ ተንሳፍፌ
ዘውድ ሆናኝ የአልማዝ አንፀባራቂዋ
በርትታ አበርትታኝ ጠንክራ በእምነትዋ
የኖህ ውሀ ቢሆን ጌታ ለኔ ያላት
ግራዬን እጉድላ በለጋ እድሜ ባያት
ነገር ባልገባኝ ለት
አጥሚት ባኘኩበት
ትዝታ ሆነና ታሪካችን ሁሉ
ብቻዬን ካየሺኝ እንደ እድልሽ ሆኖ
አንቺ ነሽ ሀሳቤ ጫጫታው ተከድኖ
ከእኔና አንቺ ውጪ ላሉት ቢሆን ሚስጥር
ባርስተ ሰላምታ ህመሜን ብናገር
መቼም እንዳትረሺ ፀሎቴ ፀሎትሽ ሆኖ እንደሚቀር
ይቅናሽ እንጂ አንቺን ኑሮሽ ይሳካና
አለኝ የምሰጥሽ የኑሮዬን ዳና
አሳትመሽ ሽጪው ወይ ካንቺው አስቀሪው
መድብል ሞልቶልሻል ልቤን ስታዝዪው
እሺ ታዲያ ጊዜ የተራረፋቹ
የኔን ስሜት የተካፈላቹ
በትዳር በፍቅር አብራቹ ላላቹ
በፍፁም አእምሮን ደርሶ እያመናቹ
ልባቹን አትግፉት ትሰቃያላቹ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot