#የእንቢታሽ ሱሰኛ!
አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ...ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን አንግቼ …
እንደ አሞራ ዙሬሽ ፣ አንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ‘ዋይ ፣ዋይ
አጃኢብ ነው መቼም!
ስትሄጅ ተራመድሁ...ስትቆሚ ቆሜ
ባንቺ ስፍር ልኬት በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔ ፣ ዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራ ፣ በእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀን ልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞ ስብሰለስል ኖሬ
ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር
ቃላት ድል ነስተውሽ በኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜ ‘ለታ
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋ ትዝታሽ ተረታ።
ሚካኤል አስጨናቂ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot
አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ...ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን አንግቼ …
እንደ አሞራ ዙሬሽ ፣ አንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ‘ዋይ ፣ዋይ
አጃኢብ ነው መቼም!
ስትሄጅ ተራመድሁ...ስትቆሚ ቆሜ
ባንቺ ስፍር ልኬት በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔ ፣ ዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራ ፣ በእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀን ልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞ ስብሰለስል ኖሬ
ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር
ቃላት ድል ነስተውሽ በኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜ ‘ለታ
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋ ትዝታሽ ተረታ።
ሚካኤል አስጨናቂ
#ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ #share @Qdist
Join and share👇👇
@qdist
@qdist
@qdist
For any question& comment ለማንኛውን
ጥያቄ&አስተያየት @e_t_l_bot