Forward from: Only Clothes™
#ስውር_ብራና_ጽሑፍ Invisible letter
#በአገራችን ስውር ቀለም ወይም የምስጢር መጻፊያ የሚባል አለ ። በቀደሙት ጊዜ ሁለት ምስጢረኞች ኃሳባቸውን ሌላ ሰው ሳያውቀው የሚጠቀሙት ዘዴ ሲሆን አጻጻፋም ጥበብን የተሞላ ነው። ተራውን ነገር በአንድ ገጽ በቀለም በመጻፍ በስተጀርባው ደግሞ የሎሚውን ውሃ በንጹሕ ዕቃ ላይ ጨምቀው
እንደ ቀለም በመጠቀም የራሳቸውን ልዩ ምስጢር ይጽፋበታል።
#ምናልባት አንዱ በኃይል ተጋፍቶ ከተላኪው ሰው ጽሑፋን በመንጠቅ ቢያነበውም ተራ ነገር መስሎ ስለሚታየው መልሶ ይሰጠዋል የላከለት መምህር
ግን ምስጢሩን ስለሚያውቅ የጽሑፋን ብራና ጀርባ ጢስ ጋርዶ ሲያስመታው የተደበቀው ጽሑፍ ስለሚወጣ የመጣለትን ኃሳብ ያገኛል መልሱንም
በተመሳሳይ ዘዴ አዘጋጅቶ ይመልስለታል።
#ሁኖም የምሥጢሩን ጽሑፍ ዘዴ ያጠና ሌላ ሦስተኛ ሰው ሥውርን ጽሑፍ የሚያነበው በተመሳሳይ ስልት ስለሆነ ቀለሙም በጢስ ከጎላ በኃላ ተመልሶ
ስለማይጠፋ ተቀባዮ ምስጢራቸው መባከኑን በቀላሉ ሊረዳው ይችላል። አባቶቻችን ምስጢራ እና ጥበባትን የያዙ ብራናዎችን ከጠላት ወራሪ ኃይል
ለመከላከል ይህን ዓይነት ዘዴ በሰፊው ይጠቀሙበት ነበር ።
ETHIO፯፯፯