ኢትዮጵያ አስገራሚ እውነታዎች
✿ ኢትዮጵያ ሀገሬ ኢትዮጵያ ሀገራችሁ
ረቂቅነቷን ከቶ ታውቃላችሁ?
ሚስጥራዊነቷን ከቶ ታውቃላችሁ?
እስኪ ካነበብኩት ትንሽ ላካፍላችሁ። ኢትዮጵያ ማለት የቃሉ
ትርጉም እነዚያ አዕምሯቸውን የታወሩ ጠላቶቿ እንደሚያወሩት
የተቃጠለ ፊት ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ ማለት ልዩ ነው
ትርጉሙ። ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ”
ማለት ነው። ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን
ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
ኢትዮጵያ ማለት እኔና እናንተ በምናውቃት ልክ ብቻ ያለች ሀገር
አይደለችም። ኢትዮጵያ ማለት ከምድር ሀገራት ሁሉ እጅግ
ምስጢራዊና ረቂቅ ሀገር ናት። ይሄን ስላችሁ ደግሞ በግምት
ወይም በስሜት ተገፍቼ አይደለም። በብዙ ማስረጃዎች ነው
እንጅ። ይሄን ጽሁፍ ስታነብቡ ውስጣችሁ የማይቀበልላችሁ፣
የኢትዮጵያ ነገር የማይዋጥላችሁ፣ ተራ አሉቧልታ ወይም አፈ
ታሪክ የሚመስላችሁ፣ ኅሊናችሁ በጠባብነት በዘረኝነት ወይም
በገንዘብና በክህደት የታወረ ጥቂት ኢትዮጵያዊያን ትኖራላችሁ።
አልፈርድባችሁም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ማንነት
አልገባችሁምና ነው። የምዕራባዊያንን ሴራ አልተረዳችሁትምና
ብታናድዱኝም አልፈርድባችሁም። አይናችሁ ፊት ለፊታችሁ
ከሚገኘው ነገር ውጪ ያለውን እውነት ስላላሳያችሁ ግን
አዝናለሁ።
(((((ብሉይ ኪዳን)))))
1ኛ) ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው
ኢትዮጵያዊው ዮቶር ነው። ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ
መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው። ቴዲ
አፍሮ በጥቁር ሰው አልበሙ ላይ የዮቶርን ኢትዮጵያዊነት
ለመጥቀስ ሞክሯል። አዎ የዮቶር እርስት ውብ ሀገር ኢትዮጵያ
ነች።
2ኛ) አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት ሲጳራ ኢትዮጵያዊት
ነች። ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። ሙሴ ይቺን
ሐበሻዊት ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም
ያጉረመርሙበት ነበር። እግዚአብሔርም ገሰፃቸው።
3ኛ) አብርሐምን የቀባው የክርስቶስ ምሳሌ የሚባለው
የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው። ይህ ካህን
በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ
ይቆጠራል።
4ኛ) በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ
ሀገር ኢትዮጵያ ነች። ይሄንን ቦታ ምዕራባዊያንና አንዳንድ
የምስራቅ ሀገራት ለመውሰድ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው
ታሪክ ይዘክራል።
5ኛ) ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ
ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ/ቤተ ክርስትያን/ ውስጥ
ነው። ይሄን ቋንቋ እኛ የቋንቋው ባለቤቶች ብናቃልለውም ቅሉ
ዓለም ግን እጅግ የሚያከብረው ትልቅና ቀዳሚ ልሣን ነው።
ይሄንን ደግሞ ራሳቸው ምዕራባዊያን ይመሰክራሉ። በዚህ ቋንቋ
ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምስጢራት ተከትበዋል።
6ኛ) ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ ኖኅ የተቀበረው
ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው። የሰው ልጅ ከሰማይ ከተጣሉት
መላዕክት (ኔፍሊሞች) በተማረው ምድራዊ ጥበብ ምክንያት
ልቦናው ከፈጣሪው ራቀ። ለምሳሌ ኮኮብ ቆጠራ፣ በአንገት
የሚታሰሩ በጆሮ የሚንጠለጠሉ በእጅና እግር ጣቶች የሚታሰሩ
ከንፈርንና ገላን የሚቀቡ ሁሉም ምድራዊ ጌጣጌቶች የመጡት
ከወደቁት መላዕክት ወይም ከኔፍሊሞች ነው። እነዚህ መላዕክት
የሰውን ልጅ ከፈጣሪው እንዲርቅ ዝሙትን፣ መዳራትን፣ ያለ
አግባብ መብላትና መጠጣትን አስተማሩት። በዚህም ምክንያት
የሰው ልጅ ኅልቆ መሳፍርት ሀጢያትን በመስራቱ እግዚአብሔር
ምድርን በንፍር ውኃ መላት። ሁሉም አለቁ። ኖኅና ቤተሰቦቹ
ብቻ ቀሩ። ይህ ሰው መቃብሩ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
7ኛ) ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን
ያሳረፋት ኢትዮጵያ/ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ
ነው።
8ኛ) የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህሪያተ
ስጋ ነው። ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና
ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት አንዳንዶች
አዳምና ሄዋን ኢትዮጵያዊያን ናቸው ይላሉ። እውነት ነው።
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች። ያች በቁፋሮ የተገኘች የዝንጀሮ
አጽም ድንቅነሽ (ሉሲ) ስለተገኘችባት ሳይሆን የእግዜር የእጁ
ሥራ የሆነው አዳም ስለተገኘባት ነው።
9ኛ) ከገነት ከሚመነጩና ገነትን ከሚያጠጡ አራት አፍላጋት/
ምንጮች/ ትልቁ ግዮን ኢትዮጵያዊ ነው። ግዮን ከገነት
ይመነጭና ወደ ምድር ይፈሳል። ከዚያም የኢትዮጵያን ምድር
ይከባል። ይህ ወንዝ ጎጃም ውስጥ ሰከላ አካባቢ ግሽ ዓባይ
የተሰኘ ቦታ ላይ ነው የሚፈልቀው። ከዚያም ሙሉ ጎጃምን
እንደመቀነት ይዞርና ወደ ኔፍሊሞች መንደር ግብጽ ይፈሳል።
10ኛ) ሞትን ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደውና
አዕምሮውን መቶ በመቶ(100%) የተጠቀመበት ብቸኛው
የምድራችን ሰው ሄኖክ ሐበሻ/ኢትዮጵያዊ/ ነው። እስከዛሬ ድረስ
አዕምሮውን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመ ምድራዊ ሰው የለም።
የሰው ልጅ የአእምሮው ልዕልና የሚለካው በምድራዊ እውቀት
ሳይሆን በሰማያዊ ጥበብ ነው። ሰው የአዕምሮው ልዕልና (IQ)
ሲያድግ ወደ ቅድስና ደረጃ ይሸጋገራል እንጅ ምዕራባዊያን
እንደሚሉት በምድራዊ ጥበብና እውቀት አይመላም። ይሄን
ደግሞ ያደረገ ብቸኛው ሰው ሐበሻው ሄኖክ ብቻ ነው።
11ኛ) ሲዖልም ገነትም የሚገኙት በመላኩ 15 ክንድ ከምድር
ከፍ ብለው ኢትዮጵያ (አፋር ኤርታሌ እና ጎጃም ጣና አካባቢ
በቅደም ተከተል) ነው። በድሮው ወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው አፋር
ውስጥ የሚገኘው ኤርታሌ የሚባለው ቦታ የራሱ ሰማያዊ
ምስጢር አለው። እዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው እሳተ ገሞራ ወይም
የእሳት ባህር ሉሲፈር (ሳጥናኤል) የታሰረበት ቦታ መሆኑን
አንዳንድ መዛግብት ላይ ለማንበብ ችያለሁ። አዎ ይህ ቦታ
የሲኦል መገኛ እንደሆነና ጎጃም የሚባለው ሀገር ላይ በተለይም
ደግሞ ጣና ዙሪያ የገነት መገኛ ናቸው።
12ኛ) በዓለም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት የዘመን ስሌት ያለው
ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ነው። ይህ የዘመን ስሌት
ምንም እንኳን አጽዋማትና በዓላት የሚከበሩበት ቀመር
በግብጻዊያን ጳጳሳት ሴራ የተበረዘ ቢሆንም የቀራትና የቀናት
ብሎም የዓመታት ስሌቱ ትክክለኛ ነው። በዓላት ስል ለምሳሌ
ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው ታኅሳስ 29 ሰኞ ቀን ከሆነ በአመቱ
ልደቱ መከበር ያለበት በዚሁ ቀን መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ
ዘንድሮ ልደቱ ሰኞ ተከብሮ በዓመቱ ደግሞ ሮብ መከበር
የለበትም። ክርስቶስ የተሰቀለው ሚያዚያ 27 ከሆነ ስቅለቱ
በየዓመቱ ከዚህ ቀን ውጪ መሆን የለበትም። በዚህ ስሌት ላይ
የፍሬሜሰኖች እጅ እንዳለበት የሚጠቁሙ መረጃዎችን
አንብቤያለሁ። ምናልባት ይሄን የበዓላትና የአጽዋማት ማውጫ
ቀመር የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሊቃውንት ቢመረምሩት የሚገባ
ይመስለኛል። እንዴት ቅዳሜ የተወለደ ሰው ልደቱ ሰኞ
ይከበራል?
13ኛ) በነብያት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለች
ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች። አዎ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ
እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መመኪያዋም አለኝታዋም እርሱ
ነውና። ይች ሀገር ከፈጣሪዋ ጋር ልዩ ትስስር ያላት የዓለማችን ብቸኛ ሀገር ነች። ፈጣሪ በስጋ የተመላለሰባት እስራኤል እንኳን የኢትዮጵያን ያክል ክብር የላትም፡፡
ከዳንኤል እይታወች፡፡
@tamzux