ከአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የተሰጠ መግለጫ
ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመው ጭፍጨፋ የሕዝባችንን ትግል አይቀለብሰውም!!!
መንግሥት መር ጭፍጨፋው በሕዝባዊ የፋኖ ትግል ይቀለበሳል!!!
ፋሽስቱና ደም የጠማው የጠራራ ጋኒን አብይ አህመድ በሕዝባችን ላይ የከፈተውን መንግሥታዊ ጦርነትና እየፈፀመ ያለውን የዘር ማሳሳት፣ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት የሰማይ አምላክ ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ በተለይ ኢትዮጵያዊያን የተረዱት ጉዳይ ነው ብሎ ማሰብ ያስቸግራል። አምባገነኑ የብልፅግና ቁንጮ፣ የኢትዮጵያዊያን የዘመናችን ታላቁ መርገም አብይ አህመድ ሲፈልግ በምድር ጦር፣ ሲፈልግ በሰማይ ጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ሁለንተናዊ ፍጅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዐይንና ጀሮ ሳይሰጠው እንደቀልድ ሁለት ዓመት እያለፈው ነው።
የአማራ ሕዝብ በታንክና በመድፍ እንዲሁም በጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት የሚጨፈጨፍበት መሠረታዊ ምክንያት የሰው ልጅ በዴሞክራሲያዊው ዓለም ሊከበሩለት የሚፈልጋቸውን ልዩና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም የመንገድና መብራት፣ ፋብሪካና ዘመናዊ ከተሞች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም በምከፍለው ግብር ልክ ልዩ ልዩ የጤናና የትምህርት ተቋማት ይከፈቱልኝ ስላለም አይደለም! የአማራ ሕዝብ የመብትና የኑሮ ማሻሻያ ጥያቄዎችን ይዞ ሳይሆን የወጣው ሰው ተብሎና ሰው ሆኖ መኖር በመከልከሉ የሕጋዊ ሰውነት እውቅናን፣ የሕግዊ ሰውነት ውክልናን እንዲሁም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በሕይወት መኖር መቻልን ለመጠየቅ የወጣ ህዝብ ነው፤ መንግሥታዊ ጦርነት የተከፈተበትም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በሕይወት መኖርን ስለጠየቀ ብቻና ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ውሎች ሁሉንም ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱና በሰውነቱ ልክ ይወቁት፣ ይዳኙት፤ እኔንም ሕጋዊ የዜግነት እውቅናና ሕጋዊ የሕዝብ ውክልና ይስጡኝ፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋርም እኩል ይዳኙኝ የሚል የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ነው። በሕዝባችን ጥያቄ ውስጥ በሀገራችን መንግስት በዘራችን ምክንያት ማንነታችን ሳይከዳ፣ ማንነታችን ሳይሳሳና ሳይጠፋ በሕግ ታውቆ መኖርን፣ እኩልነትን፣ ዲሞክራሲንና ፍትሕን የምናገኝ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መሠረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ግን ልብ ያሉት አይመስልም።
የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ሕዝብ ጨፍጫፊውና ጦረኛው አብይ አህመድ ግን እነዚህን የከበሩ የሕዝብ ጥያቄዎች የአማራን ሕዝብ በማንበርከክ ጥያቄዎቹን ድጋሜ እንዳይነሱ ማድረግ ካልሆነም የአማራን ሕዝብ ማጥፋትን ዓላማዬ ብሎ መያዙ ገሃድ የወጣ ሐቅ ነው። በአንዳንድ ፀሐፍት አምባገነኑ ሦስተኛው የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ኤዲ አሚን ዳዳ ዘር መርጦ የሰውን ልጅ ስጋና ደም ላልተገባ ተግባር ያውላል ተብሎ እንደተጻፈው ጭራቁ አብይ አህመድን የአማራን ሕዝብ ለማንበርከክ ብሎ በከፈተው ጦርነት የአማራን ልጅ ስጋና ደም እየተመገበ ያለ ሰው በላ መሆኑን ኢትዮጵያውያንም ሆነ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊገነዘበው የሚገባ እውነት ነው። የአማራ ሕዝብ በማንኛውም የታሪክ አጋጣሚ በሀገሩ መሪና መንግሥት በዚህ ልክ የዘር ጭፍጨፋ ደርሶበት አያውቅም። ፋሽስቱ የጣልያን ወራሪ ክ1928 -33 ዓ.ም ካደረሰው በደል በማይወዳደር መልኩ በሕዝባችን ላይ በዚህ አምሳ ዓመት የደረሰበት በደል የላቀ ሲሆን የሀገር ልጅ በሆነው አብይ አህመድ የደረሰበት በደል ግን የሁሉ ቁንጮ ሆኖ በገሀድ የምናየው ጉዳይ ነው። የአማራን ሕዝብ ባሪያ አደርገዋለሁ ብሎ ቆርጦ የተነሳው አባገነን የገባበት ቅጀት ውስጥ ለመውጣት የሰላም ነጋሪት ቢጎሰምለትም መንቃት የሚፈልግ አይደለም።
ሰሞኑን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)ን የጠቅላላ ጉባዔ ዓመታዊ ስብሰባን አደናቅፋለሁ ብሎ በማሰብ አመራሮቹ በሌሉበት በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በጀትና በድሮን የፈፀመው የንጹሓን ጭፍጨፋ የዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። አማራ መሆናቸውን የማያውቁ ሕጻናት በአብይ አህመድ የግል ንብረት በሆነው አየር ኃይል አማራ ተብለው ተጨፍጭፈዋል።
በእርግጥ የተሸነፈ ስነ ልቦና ባለቤት የሆነውና የስልጣን ጥሙ ከአካሉ የሚገዝፍበት - ከአዕምሮው የሚሰፋበት ይህ የዘመኑ የአፍሪካ አባገነኖች ቀንዲል ከምድር ጦር በዘለለ ሰው አልባ አውሮፕላንና ጀት የሚጠቀመው የሽንፈት ፅዋውን እየተጎነጨ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር ጭፍጨፋ ሕዝባዊ ትግላችንን አይቀለብሰውም፤ የተከፈተብን መንግሥት መር ጦርነትም እንደሕዝብ መደራጀታችንን፣ መታጠቃችንን፣ አምባገነናዊ የብልፅግና ሥርዓትን ማስወገዳችንን አያስቀረውም። ሥርዓቱ በሕዝባችን ላይ የሚፈፅመው በደል ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ የሚያበረታን እንጅ ክንዳችንን የሚያዝለው አይሆንም።
ስለሆነም ይህንን የአብይ አህመድን ሰይጣናዊ ተግባር ለመቀልበስ በቤተ አማራ (ወሎ) የምንገኝ ፋኖዎች በቀን 14/05/2017 ዓ.ም ወደ አንድነት መምጣታችን ይታወቃል። በመሆኑም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የመጀመሪያውን የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባውን በማድረግ በስኬት ያጠናቀቀ ሲሆን የማዕከላዊ ምክር ቤትንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውንም አዋቅሯል፤ በሥራ አስፈጻሚና በልዩ ልዩ መምሪያዎች ደረጃ የተመደቡ አመራሮችና ምደባውም የሚከተለውን ይመስላል።
1.ዋርካው ምሬ ወዳጆ --------ሰብሳቢ
2.አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ ------ምክ/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
3.አርበኛ ሀብታሙ ደምሴ -----ምክ/ወታደራዊ አዛዥ
4.ኮሎኔል አባይ ባየው--------ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ
5. አርበኛ በለጠ ሸጋው ------ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
5.1. ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ ----ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
6.ሺ ዓለቃ ያረጋል አሰፋ-----ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
6.1. አምሳ ዓለቃ ሲሳይ ገላነው---ምክትል ኃላፊ - ለሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ
6.2. ዶ/ር አቡበክር ሰይድ---ምክትል ኃላፊ - ለጤና ጉዳይ
7.መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ---ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ
7.1.አርበኛ ሞላ ሰማው ------ምክትል ኃላፊ - ለስንቅና ትጥቅ ስርጭት
7.2. አርበኛ ኢሳይያስ መልኩ----ምክትል ኃላፊ - ለኦርዲናንስ ክፍል
7.3. አርበኛ ኑረዲን አበበ ----ምክትል ኃላፊ - ለትራንስፖርት ስምሪት
8.መቶ ዓለቃ ዮሴፍ አስማረ ---ወታደራዊ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
8.1. አርበኛ ጌታቸው ሲሳይ ----ምክትል የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
9.አርበኛ ** ---ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ኃላፊ
10. አምሳ ዓለቃ አደም አሊ ----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን (ስርጸት) መምሪያ ኃላፊ
10.1.አርበኛ ሙላት አላምረው-----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን መምሪያ ምክ/ኃላፊ
10.2.አርበኛ ተመስገን በቀለ ----የኪነትና መዝናኛ ክፍል ኃላፊ
11.አርበኛ ተሾመ ፈንታዬ -----ልዩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
12.ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ -----ወታደራዊ አማካሪ