አትቸኩል ❗️
💍
ሰባኪው አዲስ ተጋቢ ሙሽሮችን ወደ መድረክ ጠርቶ የጋብቻ ስነ ስነርዓታቸውን እያስፈፀመ፦
“ይህንን ጋብቻ የሚቃወም ካለ ወደ መድረክ ይምጣ አለ!”
በዚህ ጊዜ አንድ የ 3 ዓመት ህፃን ልጅ ያቀፈች እርጉዝ ሴት ከአዳራሹ መጨረሻ ወንበር ተነስታ በእርጋታ ወደፊት መጓዝ ጀመረች። ሙሽሪትም ያች ህፃን የያዘች እርጉዝ ሴት ወደፊት ስትመጣ ስታይ ሙሽራውን፦
“ ወራዳ ልክስክስ በሚስትህ ላይ ነው ልታገባኝ የነበረው?” አለችና በጥፊ መታው በጎን ያለውን በር ከፍታ እየሮጠች እና እተራገመች ሄደች። አብዛኛው ታዳሚ በተፈጠረው ክስተት ተገርሞ እያጉረመረመ እና እርስበርስ እያወራ በሚቀርበው በር እየወጣ ሄደ። ያች ህፃን የያዘች ሴት ፊት ወንበር ላይ ስትደርስ ከአንዱ ወንበር ላይ ቁጭ አለች። ሰባኪውም ግራ ተጋብቶ፦
“ምነው ችግር አለ እህቴ?” ሲል በታላቅ ትህትና ጠየቃት!
ሴትዮዋም “ኧረ ምንም ችግር የለም ጌታዬ! ትንሽ የመስማት ችግር ስላለበኝ በደንብ እንዲሰማኝ ከፊት ልቀመጥ ብዬ ነው አባቴ!” ስትል መለሰችላቸው!...
የነገሮችን ፍፃሜ በደምብ ሳናጣራ በመሰለኝና በደሳለኝ (Rule of thumb) ቸኩለን በግምት ድምዳሜ ላይ ከመድረስ እንቆጠብ። ማስተዋል አለመቻላችን እና መቸኮላችን ብዙ ነገር ያሳጣናል።
© Author፡ Unknown
[ሸጋ ቀን ተመኘሁላችሁ 🙏]