ፍርድ ቤቱ የሂጃብ እገዳ እንዲቆም ያሳለፈውን ውሳኔ ያልተቀበሉ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ አዘዘ!!
የአክሱም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የሚከለክለውን መመሪያ በማገድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ያልተቀበሉ የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ አዘዘ።
ፍርድ ቤቱ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው የእስር ማዘዣ ከ2ኛ እስከ 5ኛ የተጠቀሱ ተከሳሾች “የፍርድ ቤቱን ግልፅና ህጋዊ ሥርዓት ሆን ብለው በመጣስ” የፈጸሙት ድርጊት “የፍርድ ቤቱን ስልጣን የሚያዳክም ነው” በማለት ከሷል።
የወረዳ ፍርድ ቤቱ በማዛዣ ደብዳቤው የፍትሃብሄር ህጉን አንቀጽ 156 (1) በመጥቀስ በፍትሐብሔር ክርክር ውስጥ ያለ ማንኛውም ተከሳሽ ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ያላከበረ እና የጣሰ እንደሆነ አግባብነት ባለው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌ ተጠያቂ እንደሚሆን አመልክቷል።