በጀርመን የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ
#Ethiopia | በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ አንዲት ወፍ ጎጆዋን ቀልሳ መኖር ከጀመረች ከራርማለች።
ይህች ወፍ እንደሌሎች ዝርያቸው በመጥፋት አደጋ ላይ ከሚገኙ የወፍ ዓይነቶች አንዷ ናት። የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩ የሕንጻ ማስፋፋት ሥራ ለማከናወን በተሰናዳበት አጋጣሚ በጣሪያው ጎጆዋን ቀልሳ የምትኖረውን ወፍ ይደርሱባታል። ክሊኒኩም በማስፋፋት ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ይገታል።
250 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣው ፕሮጀክትም ለዘጠኝ ዓመታት ባለበት ቆመ። በአካባቢው የሚገኘው ደን ጥበቃውም ቀጠለ፤ ወፏም ያለ ስጋት በጣሪያው ላይ ትኖር ጀመር። የወፎን ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ታዲያ ድንገት ወፏ ትሰወርባቸዋለች።
ዘሯ ሊጠፋ ነው የተባለላት ወፍ አለመኖር ግን ወዲያው የታቀደውን የሕንጻ ማስፋፋት ፕሮጀክት መጀመር አላስቻለም። በጥንቃቄና በትዕግሥት ወፏ ወደ ቀለሰችው ጎጆዋ ትመለስ ይሆናል በሚል ተጠበቀች።
ጉዳዩ የግዛቷ ፖለቲከኞችና ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ድመት በልቷት ይሁን ወይም አካባቢውን ለቃ ባልታወቀ ምክንያት የወፏ ከጎርጎሪዮሳዊው 2022 ጀምሮ አለመታየት በደስታ የማስፋፋት ሥራውን ለመጀመር አላጣደፈም። ይልቁንም የለመደችው አካባቢ ነውና ተመልሳ ብትመጣ ጎጆዋ ከፈረሰ የት ትገባለች የሚል ክርክር አስነሳ።
የከተማዋ ከንቲባ ወፏ አሁን እኛ ሳናባርራት ቦታውን ስለለቀች ሥራው መቀጠል ይችላል ቢሉም የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ሕግ ባለሙያዎች ግን አንቀጽ እየጠቀሱ ሞገቱ። የአእዋፍ ጥናት ባለሙያዎችም በዚህ እየተሳተፉ ነው።
ይህች ወፍ ፈጣሪ አድሏት ጀርመን ሀገር በመኖሯ ጎጆዋ ሳይፈርስ የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጓተተ።
Via #DW
https://t.me/Tamrinmedia