የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን ጉዳይ ላይ ይወያያል ተብሏል።
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በሱዳን ባስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም እንዲደረግ በረቀረበለት ሰነድ ላይ ዛሬ ይወያያል።
ብሪታኒያና ሴራሊዮን በጋራ ያቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ፤ ተፋላሚ ወገኖች ባስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙ፣ ንግግር እንዲጀምሩና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚጠይቅ ነው።
የውሳኔ ሃሳቡ፤ ሁለቱም ወገኖች ንጹሃንን ከጥቃት ለመጠበቅ ቀደም ሲል የገቧቸውን ቃል ኪዳኖች እንዲያከብሩ፣ ጾታዊ ጥቃትን እንዲከላከሉ፣ ያልተቋረጠ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲገባ እንዲያደርጉ ጭምር ይጠይቃል።
አባል አገራት ግጭቱን ከሚያባብስ ጣልቃ ገብነት እንዲቆጠቡ፣ በዳርፉር ላይ የተጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲያከብሩ እንዲሁም ተፋላሚዎቹ ተኩስ አቁም ላይ የሚደርሱ ከሆነ የተመድ ዋና ጸሃፊ የስምምነቱን ተፈጻሚነት የሚቆጣጠር አካል እንዲሰይሙም ጥሪ ያደርጋል
https://t.me/Tamrinmedia