ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የምርጫ ውጤቱን እንደሚቀበሉ ኣስታወቁ፡፡
ባለፈው ሳምንት በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ መደረጉ ይታወሳል።
በከፍተኛ ብልጫም የተቃዋሚው ዋደኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ (ኢሮ) ምርጫውን አሸንፈዋል።
በምርጫው የተሸነፉት ተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ "የምርጫውን ውጤት እንቀበላለን" ብለዋል።
ለተመራጩ ፕሬዜዳንትንም "እንኳን ደስ አልዎት!" ብለዋቸዋል።
“ሰላማዊና የተረጋጋ የስልጣን ሽግግር እንዲደረግ ለማድረግ የተሟላ ድጋፌን አደጋለሁ " ሲሉም ቃል ገብተዋል።
6ኛው የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አብዲራህማን ኢሮ በበኩላቸው÷ "ማንም ተሸናፊ ማንም አሸናፊ የለም ያሸነፈው የሶማሌላንድ ህዝብ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሶማሌላንድ እራሷን እንደ ሉዓላዊ ሀገር ምትቆጥር ናት፤ እጅግ ሰለማዊ፣ የተረጋጋ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማድረግ እና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማድረግም ትወደሳለች።
https://t.me/Tamrinmedia