ጀዋር መሐመድ ለቢቢሲ
ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል።
ጃዋር መሃመድ ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።
ቢቢሲ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን እንደመጡ ብዙ በጎ ነገሮች በንግግርም፣ በተግባርም ታይቶ ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ የትግራይ ጦርነት ተከሰተ፤ አሁንም በኦሮሚያ እንዲሁም በአማራ ክልሎች ግጭቶች እንደቀጠሉ ነው። ረሃብ፣ መፈናቀል እንዲሁም የከተማ ኑሮ ውድነት የአገሪቱ ገጽታ ሆኗል። በአንተ እምነት ኢትዮጵያ መስመር ስታ እዚህ ውስጥ የገባችው የቱ ጋር ነው?
ጃዋር፡- ዐቢይ ከመጀመርያውም መስመር ላይ አልነበረም። . . . [መጀመርያ አካባቢ] እኛ ከህወሓቶች ጋር እንደራደር ነበር፤ ስልጣን እንደሚለቁ፤ ማዕከላዊ ስልጣን እንደሚለቁ፣ ስምምነት ላይ ከደረስን በኋላ፣ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ማን ይሁን? የሚለው ሲመጣ የዐቢይ ስም በመምጣቱ አነጋግሬው ነበር።ያኔ ለእኔ ግልጽ ነበር።
ኢትዮጵያ ከኢህአዴግ አንድ ፓርቲ አገዛዝ፣ ወደ መድብለ ፓርቲ፣ ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መሄድ፣ መሻገር ነበረባት፤ ወደ ግጭት የማያደርስ ያለው ብቸኛ አማራጭ እርሱ ብቻ ነበር።
ገና ስልጣን ሳይይዝ፣ገና ስሙም ሳይታወቅ፣ለእኔ ከእርሱ ጋር በነበረኝ ውይይት የዲሞክራሲ ስርዓት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ግልጽ ነበር።አምባገነናዊ ስርዓትን ከአንድ ፓርቲ ወደ አንድ ግለሰብ የማሻገር ህልም እንዳለው ለእኔ ግልጽ ነበር። ለዚያ ነው የተቃወምኩት።
በወቅቱ ግን ሰዉ የሚያየው ነገር የለውጥ ስሜቱ ወያኔ [ህወሓት] ብቻ ትጥፋ እንጂ ማንም ይምጣ የሚለው ስሜት በጣም ጠንካራ ስለነበር እኔ ሰዉን ማሳመን አልቻልኩም። መጀመርያ ኦህዴዶችን፣ ቀጥሎ ሕዝቡን ማሳመን አልቻልኩም። በዚያ ምክንያት አቆምኩ እንጂ ለእኔ በጣም ግልጽ ነበር።
ከዚያ በኋላ የመጀመርያው አንድ ዓመት ሲደረግ የነበረውን ሳየው ነበር። ተወያይተን ይህንን ሽግግር እንምራ የሚለው ሲመጣ እኔ አሻግራችኋለሁ ማለት፤ የጋራ ፍኖተ ካርታ ይምጣ ሲባል አያስፈልገንም የሚል ምላሽ ተሰማ።በጎ በጎው በሚታይበት ወቅት ራሱ በውስጥ በውስጡ ወደ ዲሞክራሲ የሚያሸጋግረው ኃዲድ ተስቶ ነበር። መጨረሻ ላይ የለየለት ወደ ምርጫ ሲገባ፣ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው የሚታሰቡ ኃይሎችን ወደ መምታት ሲገባ ነው ሰዉ የነቃው እንጂ ከጅምሩም ዐቢይ ኢትዮጵያን ወደ ዲሞክራሲ የማሻገር ፍላጎት ፈጽሞ ኖሮት አያውቅም።
ቢቢሲ፦በአገሪቱ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነቶች እንደቀጠሉ ናቸው፤ በትግራይ ክልልም ግጭትን በዘላቂነት የማቆም የፕሪቶርያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልሆነም። . . . አሁንም ወደ ዲሞክራሲ የመመለስ፣ አገሪቱን ወደ መስመር የመመለስ እድል አለ ብለህ ታምናለህ?
ጃዋር፦ ቢጠብም እድል አለ። ግን አሁን እነ ዐቢይ በያዙት አመለካከት እና ትምክህተኛነት ወደ ትክክለኛው መስመር መመለስ የሚችሉ አይመስለኝም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን አይረዷትም። ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ብሔር ብሔረሰቦች ያሉበትን (Multi ethnic) የሆነን አገር፣ አሁን ባለው ዓለም ተጨባጭ ሁኔታ እና ኢትዮጵያ ባለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አይረዱም። ለመረዳትም ፍላጎት የላቸውም። ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የብልጽግና ደሴት የሚባል ተፈጥሯል። ዐቢይ እና እርሱ አካባቢ ያሉ ሰዎች ብቻ የሚንሸራሸሩበት፣ ሌላውን ሕዝብ ፈጽሞ ያገለለ፣ የሌላውን ሕዝብ አኗኗር የማይረዳ።
በቅርቡ [አዲስ አበባ] ሄጄ የሆነ ነገር ፌስቡክ ላይ ጽፌ ነበር። 'ሕዘቡ ጠውልጓል እነርሱ ደንዝዘዋል' የሚል፤ እውነቴን ነበር። ሕዝቡን ተዘዋውሬ አየሁት። ከተማ ውስጥ ቀንም ማታም እየዞርኩ ሕዝቡን አየው ነበር። ከዚያ ደግሞ ቱባ ቱባ ሚኒስትሮችን አገኘኋቸው።
ስለ ኢኮኖሚ ስታወራ፣ 'ኢኮኖሚውማ እንደዚህ አድጎ አያውቅም' ይሉሀል. . . በየቤቱ ማር እና ወተት በቧንቧ የሚፈስ ነው የሚያስመስሉት።
ስለ ጦርነት ስታወራ አማራ ክልል. . እነሱ እኮ ተከፋፍለዋል፤ እየጠፉ ነው። ኦሮሚያ ክልል ምንም ችግር የለም። ትግራይ የራሳቸው ጉዳይ. . . ያምኑታል ደግሞ [ጠቅላይ ሚኒስትሩን]። . . . የራሳቸውን ውሸት ያምኑታል። እነርሱ በያዙት አመለካከት ወደ መስመር መመለስ አንችልም። ነገር ግን ዝም ብለን እንመለከታለን? ዝም ብለን ደግሞ አንመለከትም። አገራችን ነው ሕዝባችን ነው። የለፋንበት ነው፤ እድሜያችንን ያጠፋንበት ነው። We are not going let them take us down [ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድላቸውም]። ራሳቸው ብቻ ሳይሆን አገር ይዘው ሊወድቁ ነው። እኛ ኢትዮጵያን ሕዝቦቿ ወደ መንገድ መመለስ እንችላለን? አዎ መመለስ እንችላለን። እነሱን ግን ይመልሱናል ብለን የምንጠብቅ ከሆነ ባለፉት ስድስት ዓመታት አገሪቷን ከከተተበት መከራ ወደባሰበት ነው ይዘውን እየሄዱ ያሉት።
ቢቢሲ፦ ጃዋርን ከመታሰሩ በፊት የሚያውቁት ሰዎች መንግሥት ላይ የሠላ ትችት ሲያቀርብ ፣ ፖለቲካው ላይ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ነው ።ከእስር በኋላ ግን መሀል ላይ ያለ የአሸማጋይነት ሚና ያለውን ጃዋር ነው ያየነው። እስር ቤት አንተ ላይ ያመጣው ለውጥ ምንድን ነው?
ጃዋር፦በእስር ቤት ወቅት እኔ ብቻ እስር ቤት መሆኔ አይደለም ትልቁ ነገር። ባለፈውም እንዳልኩት እኔ ትቻት የታሰርኩት ኢትዮጵያ እና እኔ ከእስር ቤት ወጥቼ ያገኘኋት ኢትዮጵያ የተለያዩ ነበሩ።
እስር ቤት ከመግባቴ በፊት የችግር ዳመናው፣ የጦርነት ዳመናው የተሰበሰበ ነበር። ከእስር ቤት ስወጣ እሳት በየቦታው ተቀጣጥሎ ነበር። ስለዚህ እንደ አንድ ተሰሚነት እንዳለው እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ምን ባደርግ ነው አገር እና ሕዝብ ማዳን የምችለው? ብዬ አሰብኩ። ወጥቼ ወደ አክቲቭዝም እና ወደ ትችት ብመለስ በእሳቱ ላይ ሌላ ቤንዚን መጨመር ሆኖ ታየኝ። ስለዚህ ያንን ተወት ላድርገው እና ያለኝን ተሰሚነት፣ ያለኝን ትስስር፣ መስተጋብር በማማከር፣ በመገሰጽ፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡም እንዲረባረብ፣ መስራት ላይ አተኮርኩ። ከእስር ከወጣሁም በኋላ ሕዝቡንም ወደ ዲያስፖራው ሄጄ ስለ ሠላም ስናገር ከፍተኛ ተቃውሞ ይደርስብኝ ነበር። ያንን ማድረግ የምችለው እኔ ብቻ ነበርኩ።
ከትግሉ ጋር ተያይዞ ያለኝ የፖለቲካ ካፒታል ነበር።ያንን የፖለቲካ ካፒታል ውጪ አገር ሄጄ በመመንዘር፣ በወቅቱ ሕዝቡ በተለያየ ወገን ያለውን ጦር በመደገፍ በጣም ተከፋፍሎ ስለነበር፣የጦርነት ገበያ እንዲጠብ እና የሠላም ገበያ እንዲሰፋ፣ መንግሥትም ሆነ ጫካ ያሉት አማፂያን ጫና ተደርጎባቸው ወደ ሠላም ይመጣሉ በሚል ነበር ያንን ስሰራ የነበረው።
መጀመርያ ለሕዝቡ ስለ ሠላም በመናገር፣ ከዚያ ደግሞ ዲፕሎማቶቸን በመቀጠል ደግሞ የአገሪቱን ባለሥልጣናት የአማፂ አመራሮችን በማግኘት የተቻለኝን ሳደርግ ነበር። ብዙ ሞከርኩ። ግን እያየሁት የመጣሁት ነገር፣ ጊዜ ለመግዣ እንጂ አገሪቱን ወደ አጠቃላይ ሠላም፣ ሥር ነቀል ሠላማዊ ለውጥ ለማምጣት ቁርጠኝነቱም ፍላጎትም እንደሌለ፣ እንዳውም ነገሮች ረገብ ሲሉ ወደ ነበረበት ሲመለሱ ስላየሁ ይህ ነገር በዚሁ ከቀጠለ እየተባባሰ ነው የሚሄደው፤ ዝም ማለቱ እና መምከሩ፣ መለማመጡ፣ መለመኑ ብዙም አላስኬደም። . . . እኔ በዚያ መቀጠሉ ዋጋ ስለሌለው ነው።
ቢቢሲ፡- ስለዚህ ወደ ቀደመው የነቃ የፖለቲካ ተሳትፎህ ተመልሰሃል?