የዶናልድ ትራምፕ በዓል ሢመት ዛሬ ምሽት ይከናወናል
ባለፈው ኅዳር ወር የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ በዛሬው እለት በይፋ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ይሾማሉ፡፡
በዓለ ሢመታቸውን ተከትሎ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ይመለሳሉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ሁለት የፍርድ ችሎት፣ በርካታ የወንጀል ክሶች፣ ሁለት የግድያ ሙከራዎች እና በርካታ ጫናዎችን አልፈው ነው የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ሽንፈታቸውን በመቀልበስ በዓለ ሢመታቸውን የሚፈፅሙት፡፡
በዓለ ሢመታቸው ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን÷ በዋሽንግተን ዲሲ ያለውን ከባድ ቅዝቃዜ ተከትሎ ከአደባባይ ይልቅ በአዳራሽ ውስኝ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡
ትራምፕ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ታሪክ ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት መምራት የቻሉ የመጀመሪያ መሪ መሆንም ችለዋል፡፡
በፕሬዚዳንቱ በዓለ ሢመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎች እና ዲፕሎማቶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ከበዓለ ሲመታቸው ቀደም ብሎ ቲክቶክ በአሜሪካ ምድር ዳግም እንዲሰራ አድርገውታል።
https://t.me/Tamrinmedia