ካናዳ የአሜሪካ 51ኛዋ ግዛት እንድትሆን የቀረበዉን ሀሳብ በመቃወም ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ነፃነታችንን ማስጠበቅ ቀዳሚ ስራችን ነው አሉ
የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከንጉሥ ቻርልስ ጋር ካደረጉት ውይይት አስቀድመዉ እንደተናገሩት ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካናዳ 51ኛው የአሜሪካ ግዛት እንድትሆን በቅርቡ ሀሳብ ካቀረቡ በኋላ ነዉ፡፡
ትሩዶ የካናዳ ርዕሰ መስተዳድር ከሆኑት ቻርለስ ጋር ከመገናኘታቸዉ በፊት ለዜጎች “ለሉዓላዊነታችን እና ለነፃነታችን ከመቆም” የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም ብለዋል።ትሩዶ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ከግርማዊነታቸው ጋር ተቀምጦ ለመወያየት በጉጉት እጠብቃለሁ፣ እንደተለመደው ለካናዳ እና ለካናዳውያን አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንወያያለን፣ ለካናዳውያን ለሉዓላዊነታችን እና እንደ ሀገር ለነፃነታችን ከመቆም የበለጠ ጠቃሚ ነገር እንደሌለ እናገራለሁ” ብለዋል።
ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ባለፈው ወር እንደተናገሩት ትራምፕ ካናዳን ስለመጠቅለል የተናገሩት ንግግር “እውነተኛ ነገር ነው” እናም ከሀገሪቱ የበለፀገ የተፈጥሮ ሀብት ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።ትራምፕ ካናዳ 51ኛው የአሜሪካ ግዛት ለመሆን ከተስማማች የተሻለች ትሆናለች ሲሉ ደጋግመው ጠቁመዋል።
ትሩዶ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ትራም ስላደረጉት ውይይት ተጠይቀዉ ከዘለንስኪ ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል፡፡
https://t.me/Tamrinmedia