#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በአቅም ማካካሻ (Remedial) ፕሮግራም ውጤት አያያዝ ላይ ማሻሻያ አደረገ፡፡
ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ50 በመቶ በታች ውጤት ካገኙ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች መካከል የተሻለ ውጤት ያላቸውን በመምረጥ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማካካሻ (Remedial)) ፕሮግራም ተመድበው የማካካሻ ትምህርት እንዲከታተሉ መደረጉ ይታወቃል።
በዚህ መሠረት ተማሪዎቹ 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ተፈትነው ሲያልፉ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ሆነው እንዲቀጥሉ እየተደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጂ ከ30% በተቋማት የሚሰጠው ውጤት አሰጣጥ ላይ ወጥነት የሌለ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፉት ሰርኩላር ገልፀዋል፡፡
በዚህም ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% የሚሰጠው ከማዕከል እንዲሆን ተወስኗል፡፡
@tikvahuniversity