በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደረገ።
በዚህም "የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል" መንግሥት ወስኗል።
ማሻሻያው በትምህርት ሚኒስቴር የቀረበን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተወሰነ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለትምህርት ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ ተገልጿል።
በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እንዲከናወንና ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት እንዲጠቀሙበትና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር ክትትል እንዲያደርግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ክና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምፀሐይ ጳውሎስ በቀን ህዳር 25/2017 ዓ.ም የተፈረመ ደብዳቤ ያሳያል።
ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት ብቻ እንደነበር ይታወሳል።
(የማሻሻያ ውሳኔው ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መነገሩን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።)
@tikvahuniversity