ኦሕዴድ-ብልጥግናየኦሮምኛ ቋንቋ (የAfaan Oromoo) ጠላት ነው! ያውም ብቸኛው!
==============
የኦሕdead-ብልጥግናን ጠላትነት የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም:: ነገር ግን: ሁሉን ብንረሳ እንኳን: መቼም የማንረሳው አንድ ተግባር አለ:: ይኸውም የኦሮምኛ ቋንቋን (Afaan Oromooን) ይመለከታል::
ከዘመናት ትግል በኃላ: በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የፖለቲካ ስብስቦች ሁሉ: Afaan Oromoo ከአገሪቱ የሥራ ቋንቋዎች አንዱ እንዲሆን ጠቅላላ መግባባት ላይ የደረሱበት ወቅት አኤአ 2010 (2002 እኢአ?) ነበር::
ወቅቱ: የምርጫ ዓመት ነበር:: ፓርቲዎች: ፕሮግራማቸውን: የምርጫ ማኒፌስቶኣቸውን: እና የፖሊሲ ሰነዶቻቸውን እያስተዋወቁ "እኛን ምረጡ!" እያሉ ዘመቻ ሚያካሄዱበት: ከተፎካካሪዎቻቸው ጋር በሕዝብ ፊት (በቴሌቭዥን) የሚከራከሩበት ወቅት ነበር::
በዚህ ወቅት: ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሚባሉት ውስጥ:-
1ኛ) ቅንጅት (የአቶ ተመስገን ዘውዴ: የአቶ አየለ ጫሚሶ):
2ኛ) አንድነት (የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ: የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ና የወይዘሪት ብርቱካን ሚdhaቅሳ: ወዘተ ፓርቲ):
3ኛ) መድረክ የተባበለው የብዙ ድርጅቶች ጥንቅር: እንዲሁም
4ኛ) በመድረክ ውስጥ ያሉት እነሕብረት (የፕሮፌሰር መረራና የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ድርጅትን ያተተው):
ይገኙበታል::
እነዚህ ድርጅቶች ሁሉ: ብዙ ፖለቲካዊ: ማሕበራዊ: ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂካዊ ጥቅሙን በመመዘንና ከማሕበረሰቡ ያደረ-የከራረመ ፍትሓዊ የመብት ጥያቄ (ቋንቋ-ነክ ፍትህ [ወይም linguistic justice] የማግኘት መብት ጥያቄ) ጋር በማገናዘብ: ኦሮምኛ (Afaan Oromoo) ከአማርኛ ጋር የአገሪቱ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ወስነው: ይሄንኑ ለምረጡን ቅስቀሳቸው ግብኣት እንዲሆን ለሕዝብ ማሳወቅ ይጀምራሉ:: በየሚድያውም እየቀረቡ: በይፋ: ቢመረጡ ይሄንን ሃሳብ በሥራ ላይ እንደሚያውሉ ቃል እየገቡ ያስረዳሉ::
በዚህ ወቅት: አንድ ፓርቲ ብቻ " ይሄ በፍፁም መሆን የለበትም!" ብሎ ሽንጡን ገትሮ መከራከር ይጀምራል--ኦሕdead! ይሄ ፓርቲ: መከራከሪያ ነጥቡ: እንደሚከተለው ነበር:-
1ኛ. “ተቃዋሚዎች ይሄንን የሚሉት ለህዝብ አስበው ሳይሆን የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ነው" የሚል ነበር::(በአጠቃላይ ምርጫን ለማሸነፍ መንቀሳቀስ በራሱ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት/ለማስቆጠር መሆኑን ዘንግተውት ይሆን?!?)
2ኛ. ኦሮምኛ የሥራ ቋንቋ መሆኑ: “የሌሎች ሕዝቦችን መብት ይጎዳል” የሚል ነበር:: (እንዴትና ለምን እንደሚጎዳ ምክንያት አልሰጡም: ማስረጃም አላቀረቡም::)
3ኛ. ኦሮምኛን የሥራ ቋንቋ ከማድረግ በፊት "ቋንቋውን ማሳደግና ለዚህ ግብ እንዲበቃ ማድረግ ያሻል" እንጂ አሁን የሥራ ቋንቋ ማድረግ ትክክል አይደለም የሚል ነበር:: (በእነሱ አረዳድ: ኦሮምኛ ለሥራ ቋንቋነት ኣይመጥንም:: ገና አልበቃም:: "ምን ጎደለው? የክልል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ: በቋንቋው ትምህርት እየተሰጠ: ትምህርት ቤቶች: ፍርድ ቤቶች: የመንግሥት መስሪያ ቤቶች: የመገናኛ ብዙሃን ሁሉ በቋንቋው እየሰሩ: በየዩኒቨርስቲው የትምህርት ክፍል ተከፍቶለት: በዲግሪ ደረጃ እየተስጠ: ወዘተ ምን እንደ ጎደለው አላስረዱም:: በዚያ ላይ: ቀድሞውኑም የሥራ ቋንቋ ለመሆን መስፈርቱ ምን ነበረ? ለመሆኑ ኣማርኛስ ቢሆን ይሄን [የማይታወቅ] መስፈርት አሟልቶ ነው ወይ የሥራ ቋንቋ የሆነው?" የሚሉ ጥያቄዎችን አልተጠየቁም: መልስም አልሰጡ: በራሳቸው ተነሳሽነትም ኣላብራሩም::)
4ኛ. ኦሮምኛን የሥራ ቋንቋ ማድረግ የሚገባው: በሕግ ሳይሆን: በጊዜ ሂደት: ሌሎቹን ሕዝቦች በማስተማር በፈቃደኝነት ተነሳስተው የሥራ ቋንቋ ይሁን ብለው እንዲቀበሉ በማድረግ ነው የሚል ነበር:: (ሲጀመር: የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ ይሆናል ማለት ዜጎች ሁሉ ያን ቋንቋ ይናገራሉ: ወይም እንዲናገሩ ይገደዳሉ: ማለት እንዳልሆነ እንኳን አልተረዱም: አላስረዱምም:: ሲቀጥል: የመብት ጥያቄ መመለስ ያለበት በሕግ እንጂ በማሕበረሰባዊ በጎነት እንዳልሆነ: የባለመብቱ ግዴታ መብቱን መጠየቅ እንጂ: አጠቃላይ ማህበረሰባዊ የምግባር መነቃቃትን ማማጣት [trying to bring about a moral awakening in the general public] እንዳልሆነ: ባለ መብት: ከመብቱ ይልቅ ለሌሎች ምቾትና በጎ ፍቃድ ቅድሚያ የመስጠት ግዴታ እንደሌለበት: ወዘተ አልተረዱም: አይረዱም: አያስረዱም ነበር:: NB. Justice cannot wait! It cannot wait particularly until—or to make—the opponents get comfortable with it.)
----- ------ -------
እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ስንኩል ሃሳቦችን በማንሳት: ኦሮምኛ ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ቋንቋዎች አንዱ እንዳይሆን በፅኑ ተከራከሩ:: ይሄን ክርክር ሲያቀርቡም የፓርቲው ተወካዮች: በምሬት (እና ቋንቋው የሥራ ቋንቋ ይሁን ያሉትን ተፎካካሪዎቻቸውን በብዙ በማማረር) ነበር::
ይሄ ጉዳይ በተቃዋሚ ፓርቲዎች አጀንዳ ተደርጎ: ውይይት በሚካሄድበት ወቅት ኣጀንዳውንም: የቀረበውን ሃሳብም የተቃወመው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ: የያኔው ኦሕdead (OPDO): የዛሬው ኦ-ብልጥግና ነበር::
ይሄንን ተቃውሞ ሲያቀነቅኑ የነበሩትና ይሄንን ታሪክ ይቅር የማይለውን አቋም የወሰዱት ግለሰቦች ዛሬም በሕይወት (እብዛኞቹም በሥልጣን) ያሉትን እነ አባዱላ ገመዳን: እነ ጁነዲን ሳዶን: እነ ሙክታር ከድርን: እነ ሱሌይማን ደደፎን: እነDhaaባ ደበሌን: እነ ኣዳነች አቤቤን: እነ ሽመልስ ኣብዲሳን: እነደዋኖ ከድርን: እነ ብርሃኑ ፀጋዬን: እነ ዘላለምን: እነ ታከለ ኡማን: እነ ወርቅነህ ገበየሁን: ወዘተ ያካትታል::
ዛሬ ደርሰው እራሳቸውን ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ("ከውስጥ ሆነው") እንደ ታገሉ በመግለፅ የሚኮፈሱት እነዚህ ተለጣፊ-ተላላኪዎች: ከየትኛውም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይል የበለጠ የኦሮሞን ሕዝብ የካዱ: የበደሉና የታገሉት የታሪክ ህፀፆች መሆናቸው በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል::
ኦህዴድ-ብልጥግናዎች: በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ: ለኦሮሞ ሳይሆን ኦሮሞን የታገሉ: የኦሮሞ ሕዝብ ዋና ጠላቶች ናቸው:: ለኦሮሞ መብት ሳይሆን በኦሮሞ መብት ላይ የቆሙ: መብቱን የረገጡ: እኩዮች ናቸው::
ኦሕዴድ-ብልጥግናዎች: ስህተት የፈፀሙ ሳይሆን: እራሳቸው ስህተት የሆኑ ናቸው:: ኦሕዴድ-ብልጥግናዎች: ከሃዲዎች ብቻ አይደሉም:: ክህደት እራሱ (its very embodiment) ናቸው:: እነዚህ ተላላኪ ባንዳ ብቻ ኣይደሉም::: የተላላኪ ባንዳነት ተምሳሌት ናቸው::
ባይሆንማ ኖሮ: እነርሱም የኦሮሞ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ባይሆኑማ ኖሮ: ለወትሮው ብዙሃነትን የሚጠየፉ: የአገሪቱን ሕብረ-ብሔራዊ ማንነት የማይቀበሉ የሚባሉ ኃይሎች የተቀበሉትን የኦሮሞ ሕዝብ የቋንቋ ፍትሕ መብት እንዴት ኣፍ አውጥተው ይቃወማሉ? በስሙ የተደራጁለት ሕዝብ መብቱ ይከበር ሲባል: እንዴት "ኣይ ኣይገባም: መከበር የለበትም" ብለው ይከራከራሉ? አለማፈራቸውስ?