Forward from: الشباب السلفيين
🔹ሀብታም ባል ለምትፈልገው ላክላት....
«ሀብታም ፈልጊ»
አግኝቼ ባልሽቀረቀር
ሞልቶልኝ ኪሴ ባይወዛም፡
የቁስ ሀብት ምን ቢትረፈረፍ
የልቤን እዝነት አይገዛም፡
.....አውቃለሁ.....
አዕምሮሽ ጥያቄ አስልቶ፤
ለምላሽ ክብሪት ይጭራል፡
ታውቂያለሽ ከሳቅሽ ይልቅ፤
ሐዘኔ እጂጉን ያምራል...!!
ጎደሎ ከሰው ባይጠፋም፤
ቢያጋጥም የኑሮ ስንኩል፡
ችግሬ ነውር አይጠራም፤
ቢለካ ከፅድቅሽ እኩል፡
ቁስሌን አትንኪው እንጂ
ተይ እንጂ እንተሳሰብ፡
አንድ ወንዝ ያፈራን ልጆች
አይደለን እንደ ቤተሰብ!?
.....ሐቁን ግን ልንገርሽ....!?
የተፈጠርኩት ከአፈር ነው፤
ለአፈር ክብር ይሰጣል፡
አልጋዬ መሬት ቢሆንም
ገላዬ በአፈር ያጌጣል፡
እንቅልፍሽ ምቾት ቢኖረው
ህልሙ ግን የኔ ይበልጣል፡
የተናገርሽውን ንግግር፤
መቼም እንዳትዘነጊ፡
ለኔ ድህነት ሀብት ነው፤
አንች ግን ሐብታም ፈልጊ...!!
...... ሰላም ሁኝ....
በኑረዲን አል አረብ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
«ሀብታም ፈልጊ»
አግኝቼ ባልሽቀረቀር
ሞልቶልኝ ኪሴ ባይወዛም፡
የቁስ ሀብት ምን ቢትረፈረፍ
የልቤን እዝነት አይገዛም፡
.....አውቃለሁ.....
አዕምሮሽ ጥያቄ አስልቶ፤
ለምላሽ ክብሪት ይጭራል፡
ታውቂያለሽ ከሳቅሽ ይልቅ፤
ሐዘኔ እጂጉን ያምራል...!!
ጎደሎ ከሰው ባይጠፋም፤
ቢያጋጥም የኑሮ ስንኩል፡
ችግሬ ነውር አይጠራም፤
ቢለካ ከፅድቅሽ እኩል፡
ቁስሌን አትንኪው እንጂ
ተይ እንጂ እንተሳሰብ፡
አንድ ወንዝ ያፈራን ልጆች
አይደለን እንደ ቤተሰብ!?
.....ሐቁን ግን ልንገርሽ....!?
የተፈጠርኩት ከአፈር ነው፤
ለአፈር ክብር ይሰጣል፡
አልጋዬ መሬት ቢሆንም
ገላዬ በአፈር ያጌጣል፡
እንቅልፍሽ ምቾት ቢኖረው
ህልሙ ግን የኔ ይበልጣል፡
የተናገርሽውን ንግግር፤
መቼም እንዳትዘነጊ፡
ለኔ ድህነት ሀብት ነው፤
አንች ግን ሐብታም ፈልጊ...!!
...... ሰላም ሁኝ....
በኑረዲን አል አረብ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi