የጋምቤላ ክልል ለጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተጎጅዎች የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
ሐምሌ 20/2016 (አዲስ ዋልታ) የጋምቤላ ክልል በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን ገልፀዋል።
ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉ ሲሆን በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
በተከሰተው የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በማሰብ ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ በተወሰነው መሠረት በክልሉ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡