አየር መንገዱ የዓለም አራት ኮኮብ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት አገኘ
ኅዳር 9/2017 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው አፔክስ ፓሴንጀር ቾይስ አዋርድ 2025 (APEX Passenger Choice Awards 2025) የዓለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ዕውቅና እና ሽልማት አገኘ።
ይህ የዓለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች በረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጡ ድምፆች መሰረት የተበረከተና በአቪዬሽኑ ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ዕውቅና መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እውቅናውን አስመልክተው “ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የአገልግሎት ደረጃዎችን ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ነው። ጥረታችን እውቅና በማግኘቱ በጣም ደስተኞች ነን፣ ይህም ለበለጠ ስኬት እንድንጥር ያነሳሳናል” ብለዋል።