አሜሪካ በኪዬቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት ዘጋች
ኅዳር 11/2017 (አዲስ ዋልታ) አሜሪካ ሩሲያ በዩክሬን የአየር ጥቃት ልታደርስ ትችላለች በሚል ፍራቻ በኪዬቭ የሚገኘውን ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት መዘጋቷን አስታውቃለች።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ዛሬ ሩሲያ በኪዬቭ የአየር ጥቃት ልታደርስ እንደምትችል ተጨባጭ መረጃ እንዳገኘ እና ኤምባሲው በጊዜያዊነት እንደሚዘጋ አስታውቋል።
በኪዬቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ፣ ኤምባሲው የሚዘጋበት ምክንያት ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል እንደሆነ እና የኤምባሲው ሰራተኞችም የአየር ማስጠንቀቂያ በሚሰጥበት ጊዜ ከአደጋ መጠለያ ውስጥ እንዲቆዩ ማሳሰቡን አይሪሽ ኤግዛማይነር ዘግቧል።