ጋናውያን ነገ ፕሬዘዳንታቸውን ይመርጣሉ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋና ነገ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች።
ባለፉት አስርት ዓመታት ጀምሮ በአስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እየተንገዳገደች የምትገኘው ጋና በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት የስልጣን ዘመናቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣዩን ፕሬዚዳንታቸውን ለመምረጥ ቅዳሜ ዕለት ምርጫ ይካሄዳሉ።
የወቅቱ ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ የሁለት ጊዜ የስልጣን ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ 12 እጩዎች ለፕሬዚዳንትነት እየተወዳደሩ ይገኛሉ።
ነገር ግን በምርጫው ገዥው አዲሱ የአርበኞች ፓርቲ እና የተቃዋሚው ብሔራዊዊ ዴሞክራቲክ ኮንግረስ የተባሉት አውራ ፓርቲዎች ግንባር ቀደምትነት ይፎካከራሉ ተብሏል።
አሁን ላይ በምክትል ፕሬዘዳንትነት የሚገኙትን የ61 አመቱ ማሃሙዱ ባውሚያ እና በ66 አመቱ ጆን ማሃማ መካከል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚደረግ የቅድመ ምርጫ የህዝብ አስተያዬቶች ይጠቁማሉ።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው እና የቀድሞ የአንድ ጊዜ ፕሬዝዳንት ጋናን የመሩት ጆን ማሃማ ልክ እንደአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ያሸንፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሲኤንኤን ዘግቧል።