1 ሺህ 155 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
ኅዳር 27/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሳዑዲ ዓረቢያ 1 ሺህ 155 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ከህዳር 4/2017 እስከ ህዳር 27/2017 ወደ ሀገር ከተመለሱት 1ሺህ 155 ዜጎች 446 ወንዶች፣ 631 ሴቶች 78 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 218 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን ከ87 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።