ሰክሮ አካባቢን ማወክ
#ሕግ_ይዳኘኝ
ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጦችን መውሰድ ለስካር ይዳርጋል፡፡ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት የሚያስከትለው የጤና ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ሰዎች በስካር መንፈስ የመኖሪያ አካባቢያቸውን ለረብሻሉ ይችላሉ፡፡
ስካር ድፍረትን የሚሰጥ በመሆኑ የሰከሩ ሰዎች ከአልኮል ግፊት ነጻ በነበሩበት ወቅት ማድረግ የማይደፍሩትን፣ የማይፈልጉትን እና የማይችሉትን ነገሮች ለማድረግ ይደፋፈራሉ፡፡ ይጮሃሉ፤ ይረብሻሉ፡፡
ይህ ድርጊት ግን በስካር መንፈስ ስለተደረገ ብቻ ችላ ተብሎ አይታለፍም፡፡ በሕግ ያስጠይቃል፡፡ ተገቢ እና ተመጣጣኝ ቅጣትም ያስከትላል፡፡
በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 819 መሰረት ማንም ሰው ሰክሮ ወይም አዕምሮ የሚያናውጥ ነገር ቀምሶ በሕዝብ አደባባይ የሚያስነቅፍ እና የሚያስነውር ስራ የፈጸመ፣ የማስፈራራት ንግግርን የተናገረ እንደሆነ ከስምንት ቀን በማይበልጥ በማረፊያ ቤት ይቀጣል፡፡
ይሄም ሰክሮ ሕዝብን ማወክ ሲሆን ምንም እንኳን ለከባድ አደጋ የሚያጋልጥ ባይሆንም በየሰፈራችን፣ በመጠጥ ቤቶች፣ በመንገዶች እና በተለያዩ ቦታዎች ድርጊቱ በተደጋጋሚ ሲፈጸም ይስተዋላል፡፡
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 531 በተደነገገው መሰረት ደግሞ አልኮል በመጠጣት የሌላውን ሰው ጤንነት ለአደጋ ያጋለጠ እንደሆነ ከአንድ ዓመት በማይበልጥ ቀላል እስራትና በመቀጮ ይቀጣል፡፡
ይሁን እንጂ አንድ ሰው ጠጥቶ ከባድ ወንጀል ቢፈጽም የፈጸመው ወንጀል በሕግ አግባብ የሚያስቀጣውን ቅጣት ይቀበላል፡፡
በብርሃኑ አበራ