የቫላንታይን ቀን
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
3፥31 በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
በክርስትና ታሪክ ውስጥ ቫለንቲኑስ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሰዎች ሲሆኑ ከሁለቱ የመጀመሪያው በ 100 ድኅረ ልደት ግብፅ ተወልዶ በ 160 ድኅረ ልደት ቆጵሮስ የሞተው ቫለንቲኑስ የኖስቲስ መሪ የነበረው የቴዎዳስ ተማሪ ነው፥ ቫለንቲኑስ “ኢየሱስ የማርያም ዘር አይደለም” የሚል አቋም ያለው ሲሆን የእርሱ ተማሪዎች ቫለንቱሳውያን ይህንን አቋም በጥንት ጊዜ ያራምዱ ነበር።
ሁለተኛው ደግሞ በ 226 ልደት ተወልዶ በ 269 ድኅረ ልደት በሮሙ ንጉሥ በክላውዲዮስ ዘመን የተሠዋው ሰማዕት ነው፥ ይህ ሰው በዘመነ ሰማዕታት ጊዜ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር የካቲት 14 ቀን 269 ድኅረ ልደት ሰማዕት ሆኗል። እርሱ የሞተበትን ቀን በምዕራባውያን ካቶሊክ የካቲት 14 ቀን ሲዘከር በምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ ደግሞ ሰኔ 6 ይዘከራል፥ ሰማዕቱ ቫለንቲኑስ በሕይወት ዘመኑ ወቅት የሮም መንግሥት ወታደሮች እንዳያገቡ ሲከለክል እርሱ ግን የሚፋቀሩትን ይድር ነበር፥ በዚህም ንጉሡ ክላውዲዮስ አቂሞበት ነበርና በወቅቱ "ጣዖት አላመልክም" በማለት ሰማዕት ሆኗል።
በዘመናችን ያሉ ሰዎች የቫላንታይን ቀን እያሉ በዓመት አንዴ የካቲት 14 ቀን የሚያከብሩት የፍቅረኛሞች ቀን መሠረቱ ይህ ነው፥ "ቫላንታይን"Valentine" የሚለው ቃል እራሱ "ቫለንቲኑስ" ከሚባለው የክርስትና ሰማዕት እንደመጣ አንባቢ ልብ ይለዋል። እንደ ኢሥላም አስተምህሮት የምናከብረው ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ነው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፊጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አድሓ ደግሞ መሥዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم “ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ”
“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። አሏህን የምንወድ እንደሆንን ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" እንከተል፦

በተረፈ ከክርስትና ሾልኮ የመጣውን የቫላንታይን ቀን ከማክበር ሆነ ከማስከበር እንጠንቀቅ! የቫላንታይን ቀን ማክበር እና ማስከበር ግልጽ ፈሣድ ነው። አሏህ በኢሥላም ስም ፈሣድ ከሚያስፋፉ ሙፍሢዲን ይጠብቀን! አሚን።
✍ከዐቃቢ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ