"ዘር" ፍጡር እንጂ ፈጣሪ እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ማኅፀን ውስጥ ያለውን ሽል ያለ ዘርአ ብእሲ ያስገኘው አንዱ አምላክ "አብ" ሲባል የተገኘው ሰው ደግሞ "ወልድ" ተባለ፦
ሉቃስ 1፥35 "ከ-አንቺ" የሚወለደው ቅዱስ የአምላክ ልጅ ይባላል። διὸ καὶ τὸ γεννώμενον ἅγιον κληθήσεται Υἱὸς Θεοῦ.
"የሚወለደው" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ጌኖሜኖን" γεννώμενον ሲሆን "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "ሆነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚሆነው” ማለት ነው፥ "ከ" የሚለው መስተዋድድ "አንቺ" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ሆኖ መግባቱ በራሱ ኢየሱስ ከማርያም መገኘቱን ያሳያል። ያለ ወንድ ዘር በሴት ብቻ የተገኘ ብቸኛ ልጅ ስለሆነ "ሞኖጌኔስ ሁዮስ" μονογενὴς υἱός ተብሏል፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥9 አምላክ አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ὅτι τὸν Υἱὸν αὐτοῦ τὸν μονογενῆ ἀπέσταλκεν ὁ Θεὸς εἰς τὸν κόσμον.
"ሞኖጌኔስ" μονογενὴς የሚለው ቃል "ሞኖስ" μόνος እና "ጌኑስ" γένος ከሚል ሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ጌኑስ" γένος ማለት ደግሞ "የተወለደ" ማለት ነው። እንደ በጥቅሉ "ሞኖጌኔስ ሁዮስ" μονογενὴς υἱός ማለት "የተወለደ ብቸኛ ልጅ"only begotten son" ማለት ነው። አምላክ ፆታ የለውም፥ አይባዛም አይከፋፈልም። ተራሮች የተፈጠሩ ቢሆንም በፍካሬአዊ እንደተወለዱ ይናገራል፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ ተራሮችን "የሠራ"፥
መዝሙር 89(90)፥2 ተራሮች "ሳይወለዱ"፥ πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι
"ሳይወለዱ" ማለት "ሳይሠሩ" "ሳይፈጠሩ" ማለት ከሆነ እንግዲያውስ "ወልጄሃለሁ" ሲል "ፈጥሬካለው" ማለት ነው። ዓለም ሳይፈጠር በመለኮታዊ ዕቅድ ውስጥ "የወለደው" ማለት "የፈጠረው" ከማርያም ማኅፀን ነው፦
መዝሙር 109(110)፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን "ወለድኩህ"። ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.
"ጋስትሮስ" γαστρὸς ማለት "ማኅፀን" ማለት ሲሆን ፈጣሪ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ በመለኮታዊ ዕቅድ ከማርያም ማኅፀን እንደፈጠረው ያሳያል። ግዕዙ "ከርሥ" ሲለው "ማኅፀን" ማለት ነው፥ ማኅፀን ውስጥ "የሚያስሆን" አምላክ ሲሆን "የሚሆን" ደግሞ ሰው ነው። "ወለደ" ማለት "ፈጠረ" በሚል የመጣ ነው፦
ዘዳግም 32፥15 የፈጠረውንም አምላክ ተወ። וַיִּטֹּשׁ֙ אֱלֹ֣והַ עָשָׂ֔הוּ
ዘዳግም 32፥18 የወለደህን አምላክ ተውህ። וַתִּשְׁכַּ֖ח אֵ֥ל מְחֹלְלֶֽךָ
ዐውዱ ላይ መወለድ መፈጠርን ለማመልከት ከመግለጽም በተጨማሪ አንዱ አምላክ ለእስራኤል "አባት" የተባለው "ፈጣሪ" የሚለው ቃል ለማሳየት ነው፦
ዘዳግም 32፥6 የገዛህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህ እና የመሠረተህ እርሱ ነው። הֲלוֹא־ הוּא֙ אָבִ֣יךָ קָּנֶ֔ךָ ה֥וּא עָֽשְׂךָ֖ וַֽיְכֹנְנֶֽךָ׃
በዕብራይስጥ "አብ" אָב ማለት በተመሳሳይ "አባት" ማለት ሲሆን "የፈጠረህ" የሚለው የግሥ መደብ በራሱ አምላክ "አባት" የተባለው ስለፈጠረ መሆኑን በግልጽ ተቀምጧል፦
ኢሳይያስ 1፥2 ልጆችን "ወለድሁ" አሳደግሁም፥ እነርሱም አመጹብኝ። υἱοὺς ἐγέννησα καὶ ὕψωσα, αὐτοὶ δέ με ἠθέτησαν.
"ወለድሁ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤጌኒሳ" ἐγέννησα ሲሆን መፈጠርን የሚያሳይ ነው፥ እስራኤል "አንድያ ልጅ" የተባለው ለዚያ ነው፦
ዕዝራ ሱቱኤል 4፥58 "የምወደው የበኵር አንድያ ልጄ" ያልኸን እኛ ወገኖችህ ግን በአሕዛብ እጅ ገባን።
እዚህ ድረስ ከተግባባን መርየም፦ "ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? ስትል አሏህ በጂብሪል "አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፦
3፥47 ፡-"ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
ይህንን በቀላሉ ከተረዳችሁ ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም