#ለመረጃ
ጅቡቲ ላይ የተከማቹ የነዳጅ ተሸከርካሪዎች እንዲገቡ ተፈቀደ!
የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡
አዲሱ መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም እንዳይገቡ ታግደው የቆዩ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ከተለያዩ ኤጀንሲዎችና ከጉምሩክ ኮሚሽን ተውጣጥቶ የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ዝርዝር ግምገማ ማድረጉን ተከትሎ፣ በጥያቄ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በተገዙበት ቀንና የጉምሩክ ምዝገባ መሰረት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡
መንግሥት በተለይም ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢው ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው መንግሥት ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል (@አዲስ አድማስ)፡፡