🍀ሥራ በመንፈሳዊም በዚህ ዓለምም ያስከብራል
መንፈሣዊውንም ዓለማዊውንም ሥራ ሳትደክሙ ለምትሠሩ ለእናንተ ትልቅ አክብሮት አለኝ ምክንያቱም ሁሉም እንደ እናንተ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልመና ይቀር ነበር እነዚህ ጥቅሶች ለእናንተ ነው።
“አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ (ዮሐ 5:16)” ብሎ እንዳስተማረን እግዚአብሔር ድንቅ ነገርን ሲሠራ ይኖራል። በሥራ አንቀፅ የጀመረው መጽሐፍ ቅዱስ “እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ (ራዕ 22:12)”“ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን:- ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና:- ሥራ ከቶ ሳይሠሩ፥ በሰው ነገር እየገቡ፥ ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና (ተሰሎ 3:10)”“ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት (ገላ 6:9)”“ “ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ (ሮሜ 12:11)”“ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም። የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል (2 ጢሞ 2:6-7)”ራሱም በሰው ላይ ላለመክበድ እየሠራና እየደከመ ይኖር እንደነበር ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች “በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን (1 ቆሮ 4:12-13)”ሌሎችንም ማስቸገር እንደሌለበት ሲናገር “ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም” ( 2ኛ ተሰሎ 3፡8)
“አንተ ታካች፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂት ታንቀላፋለህ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ፤ እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል (ምሳሌ 6:7-11)”
“የትጉ እጅ ትገዛለች፤ የታካች እጅ ግን ትገብራለች (ምሳሌ 12:24)” ይልና “የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች። በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፤ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል (ምሳሌ 10:4-5)”
“ታካችን ምኞቱ ትገድለዋለች፥ እጆቹ ይሠሩ ዘንድ አይፈቅዱምና (ምሳሌ 21:25)”
“የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፤ አንዳችም አታገኝም፤ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች (ምሳሌ 13:4)” “በሥራው ታካች የሚሆን የሀብት አጥፊ ወንድም ነው (ምሳሌ 18:9-10)”ክርስቲያን በሥራ መትጋትን በምንም ሊተካው አይችልም፡፡ ምድራዊ ሀብትም ይሁን ሰማያዊ ጽድቅ በመትጋት እንጂ በመታከትና በመተኛት አይገኝም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል፤ ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ (ምሳሌ 14:23-24)” በማለት ልምላሜ (ትርፍ) በድካም (በመሥራት) እንጂ በከንፈር (በማውራት) እንደማይገኝ አስገንዝቦናል፡፡ በተጨማሪም “ምድሩን የሚያርስ እንጀራ ይጠግባል፤ ምናምንቴዎችን የሚከተል ግን ድህነት ይሞላበታል። የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም (ምሳሌ 28: 19-20)” ብሎ መትጋትን ገንዘብ እንድናደርግ አስተምሮናል፡፡ እንቅልፍን መውደድም እንዲሁ ለድህነት እንደሚዳርግ ሲናገር “ድሀ እንዳትሆን እንቅልፍን አትውደድ (ምሳሌ 20:13)” ብሏል፡፡
@felgehaggnew