"ከሚከፈልህ በላይ ስትሰራ ከምትሰራው በላይ ይከፈልሀል" ይለናል ታላቁ የስኬት ደራሲ ናፖሊዮን ሂል። 🧠
🔴አሁን የምታገኘውን ገቢ እና ውጤት አይተህ ልፋትህን አትቀንስ፤ ነገ የምትደርስበት ነው ወሳኙ። ስለዚህ ለምን አቅምህን ትሰስታለህ?
በሙሉ አቅምህ ስራ ተማር ከዛ በህይወትህ ላይ ተዓምሩን ታየዋለህ!
⚠️ነገር ግን ለስራህ ብለህ ደስታህን ማጣት የለብህም፤ የምትሰራውን ስራ በደስታ እና በፍቅር ነው ማሳለፍ ያለብህ፤ ያለ ደስታና ፍቅር የሚያልፍ ቀን ህይወት አልባ ነው።
ስኬታማ መሆን ማለት አሁን የቱ ጋር እንዳለህ ማወቅ፤ ከዛ ወደ ምትፈልግበት ጫፍ ለመድረስ የሚጠበቅብህንና ያመንክበትን እያደረክ ከሆነ ነው። ✔️አየህ ሁሌም ቀኑ አልፎ ማታ ልተተኛ ስትል እና ጠዋት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ያመንክበትን ነገር እየሰራህ፣ የሚያስደስትህን ኑሮ እየኖርክ እንደሆነ አስበህ ደስተኛ ከሆንክ ስኬታማ ነህ። ወዳጄ የስኬት ጥግ ደስተኛ መሆን ነው!✔️
ምን አልባት ሁል ጊዜ የምትሰራውን ነገር ደስ እያለህ ላትሰራ ትችላለህ፤ይህ የሆነው ደግሞ በስሜቶቻችን መለዋወጥ ነው። ስለዚህ አንዳድ ጊዜ 🔹
❌ስራ የማዘግየት፤
❌የመደበት እና
❌ስራ ያለመስራት ወይም የስንፍና ስሜት ከተሰማህ የሚጠበቅ ነገር ነው። 🔹
የሰው ልጆች ስንባል ሁሌ ቋሚ ስሜቶች አይኖሩንም።ነገር ግን እስካልጠቀመን እና ለስኬታችን ጠንቅ እስከሆነ ድረስ ልናስወግደው እና ወደ መልካሙ የአስተሳሰብ እና የስሜት ጣቢያ ውስጥ መግባት ይኖርብናል። 📌
✔️ይህን ለማድረግ ደግሞ ስለ ስሜቶችክ መረዳት እና ማወቅ ይኖርብሃል።
የተለያዩ ስሜቶችህ የሚመጡት አንተ ስትጠራቸው ሳይሆን በፈለጉበት ሰዓት ነው ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት በስሜትህ ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ ሁኔታዎች ዘርፈ-ብዙ በመሆናቸው ነው ።
➡️ይህ ሁኔታ በቀላሉ ለመገንዘብ የሚያዳግተን የተወሳሰበ ጉዳይ ሊሆን ይችላል። ስሜትህ፣ የትናንት ልምምድህ፣ የምታሰላስላቸው ሃሳቦች፣ የሰውነት "የሆርሞን" ለውጦችና የመሳሰሉት ከአንተ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ጥርቅም ነው።
➡️ወደ አንተ የሚመጡትን ሁኔታዎች ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ባትችልም፣ ለእነዚህ ነገሮች የምትሰጠውን ምላሽ ግን መቆጣጠር ትችላለህ።
🔹ለምሳሌ፣ በጥዋት መነሳትና ኮምፒውተርህን💻 አብርተህ የትሬዲንግ ቻርቱን ከፍተህ አዲስ ነገር ለማወቅ መጣር ሲገባህ ከአልጋህ ሳትወጣ ተደብተህ የቆየህበትንና፣ ከተነሳህም በኋላ ራስህን ጥለህ ምንም ሳትሰራ የዋልክበትን ምክንያት "ለምን❓" ብለህ ጠይቅና ተጋፈጠው። ይህንን አትዘንጋ፣ የእለቱ ስሜትህ ነው ተግባርህን የሚወስንልህ ተግባርህ ደግሞ እጣፈንታህን። ስለዚህ፣ "ይህንን ነገር የማደርገው ለምንድን ነው? " ብለህ ራስህን መጠየቅ ስትጀምር መንስኤውን ታገኘዋለህ።
💠ይህንን እውነታ መለማመድ ስትጀምር ስሜትህ አንተን መምራቱ እየቀነሰ ይሄድና አንተው አውጥተህና አውርደህ ሚዛናዊ እውነታ ላይ በመድረስ መምራት ትጀምራለህ ። 📊