#ተሰውፍ (ሱፍይነት) #ክፍል_2
ሱፊ የሚለው ቃል ስርወ ፍችውን እና መነሻውን ስናይ ከሶሰት ዐረብኛ ፊደላት- ሰ- ወ- እና ፈ- የመጣ ቢሆንም የዓሊሞች ኺላፍም ልዩነት አላጣውም፡፡ አንደኛው ምልከታ ሱፊ የሚለው ቃል ሰፍ ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን መስመር ወይም ድርድር ማለት ነው፡፡ በነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ መስጊድ ቀድመው የሚመጡና
በሶላት ወቅት የመጀመሪያው ሰልፍ ላይ የሚቆሙትን ያጣቅሳል፡፡
ሌላኛው ዕይታ ቃሉ ሱፋ፣ የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መስጊድ በረንዳ ማለት ነው፡፡ ሐዲሱ እንደሚለው መኖሪያ ቤት የሌላቸው ቀላል ቁጥር የሌላቸው የነቢዩ ባልደረቦች የሚኖሩበት በረንዳ ነበር፡፡
ጊዜያቸውን በአምልኮ፣ ቅዱስ ቁርአንን በመሸምደድ እና የነቢዩን ቃላት በልባቸው በመያዝ የሚያሳልፉ ነበሩ፡፡ ራሳቸውን ከዓለማዊ
እንቅስቃሴዎች ያናጠቡ በመሆናቸው ነቢዩና ባልደረቦቻቸው ፍላጎታቸውን ያሟሉላቸዋል፡፡ የመስጊዱ በረንዳ መኖሪያቸው ስለነበር አስሀቢ ሱፋ (የበረንዳ ጓዶች) ተብለው ነበር የሚጠሩት፡፡
ሆኖም አብዛኛው ምሁራን ሱፊ የሚለው ቃል የመጣው ሱፍ- ሱፍ ከሚለው ቃል እንደሆነ ያምናሉ፤ ቀደምት ፃድቃኖች ከቅንጦት ህይወት የተናጠቡ በመሆናቸው የሚለብሷቸው ልብሶች ያልቀለሙ ሻካራ በመሆናቸውነበር የሚኮሰኩሰው ልብስ ይችን ዓለም በገዛ ፈቃዳቸው ከነደስታዋ እርግፍ አድርገው እንደተዏት ምልክት ነው፡፡
https://t.me/YASIRAJEL_ALEM