ዘማሪ አገኘሁ ይደግ - [ውለታው]አዝ፦ ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
(ውለታው በዛብኝ)
ኢየሱሴ ለእኔ በመስቀል ሞተልኝ
በእንጨት ተንጠልጥሎ እርግማን ሆነልኝ
በከበረ ደሙ በውድ ዋጋ ገዛኝ
ሲጠራኝ ብቻዬን ዛሬ ግን አበዛኝ
ከአዕምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
አዝ፦ ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ (ውለታው በዛብኝ)
ከበለስ ዛፍ በታች ተቀምጬ አይኝ ተንኮል የሌለብህ የእስራኤል ልጅ አለኝ
ታማኝ አድርጐ ቆጥሮ ለአገልግሎት ሾመኝ
ኢየሱሴን መጠጋት ለእኔ እጅግ ጠቀመኝ
ከአዕምሮ በላይ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ
እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
አዝ፦ ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
(ውለታው በዛብኝ)
በግ እረኛ ነብረኩ ገና ብላቴና
እግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘሁኝና
እኔን በናቁኝ ፊት ራሴን በዘይት ቀባኝ
ንጉሡ ሊያከብረኝ ወደ እልፊኙ አገባኝ
ሰው ላደረገልኝ እንደዚህ ዛሬ
ሥሙን ላወድሰው በዝማሬ እጅግ ብዙ ነው የእርሱ ውለታ እንዴት ላመስግነው ይህንን ጌታ
አዝ፦ ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ)
እግዚአብሔር አምላኬ ድንቅ አደረገልኝ
ውለታው (3x) (ውለታው በዛብኝ) ናዝራዊው ወዳጄ ብዙ አደረገልኝ
✞በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን✞
✝️መልካም ፋሲካ✝️
➥
@Yemezimur_Maikel