♦ " ፍ/ቤቱ የፈለገውን #ውሳኔ ይወስን፤ እኔ በዚህ ዕድሜዬ በ74 ዓመቴ ለእነዚህ ወጣቶች #መልፈስፈስን አላስተምርም" !
ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ታዲዎስ ታንቱ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 12/2017 ዓ/ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ከቃሊቲ ማ/ቤት የቀረቡ ሲሆን መዝገቡ ተቀጥሮ የነበረው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ታዲዎስ ታንቱ የሚያቀርቡትን ማቅለያ ተመልክቶ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት በሚል ነበር።
ይሁን እንጅ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና በደል በማጋለጣቸው በአገዛዙ ጥርስ የተነከሰባቸው ብሎም ወደ ግዞት የተወረወሩት ታዲዎስ ታንቱ የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ወንጀል ስለሌለብኝ ማቅለያ አላስገባም፤ የመሰላችሁን ፍረዱ ሲሉ ተደምጠዋል።
በእለቱ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ታዲዎስ ታንቱ ከተናገሩት መካከልም፦
"እኔ ተፈጥሮ በሰጠኝ የማመዛዘን ሕሊና መሰረት ለተበደሉ ዘሮች ወይም ማንነቶች ላይ ሚዛናዊ ሀሳብ በመስጠቴ የጥፋተኝነት ስሜት አይገባኝም፤ በጠበቆቼ በኩል ማቅለያ ለፍ/ቤቱ እንዳቀርብ የቀረበልኝን ጥያቄ አልተቀበልኩትም፤ ምክንያቱም የቅጣት ማቅለያ ማዘጋጀት ማለት አጥፍቻለሁ የሚል የጥፋተኝነት ድምዳሜ ስለሚያሳይ ተፈጥሮ የፈቀደችልኝን መብት በሕግ አልቀይረውም፤ ውሳኔውን አልቀበለውም፤ ምክንያቱም የሰናፍጭ ቅንጣት የምታክል ወንጀል ስለሌለብኝ አልቀበለውም ብያለሁ፤ ይህ አቋሜ ነው።" ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም "ፍ/ቤቱ የፈለገውን ውሳኔ ይወስን፤ እኔ በዚህ ዕድሜዬ በ74 ዓመቴ ለእነዚህ ወጣቶች መልፈስፈስን አላስተምርም" በማለት አቋማቸውን በድፍረት አሳውቀዋል።
በዳኞች በኩልም ማቅለያ አለማስገባት ጉዳት እንዳለው ጠበቆች ሊያስረዷቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም በቀደመ ቀጠሮአቸው ጥፋተኛ በተባሉባቸው በ3 ክሶች ላይ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለጥቅምት 15/2017 እንዲቀርቡ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ታውቋል።
✍️ ይድነቃቸው ከበደ