በመቐለ ከተማ ሰላሚዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ዛሬ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ከመቐለ እና አከባቢዋ የተወጣጡ ወጣቶች በጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሾሙ ከንቲባ ስራ እንዲጀምሩ ያለመ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ወጣት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ህጋዊው ከንቲባ ወደ ፅህፈት ቤታቸው ሳይገቡ ከቦታው ንቅንቅ እንደማይሉ ፤ ከተማዋ የግርግር እና ረብሻ ምንጭ እንድትሆን እንደማይፈቅዱ ድምፃቸው በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
መቐለ ከተማ በጊዜያዊ አስተዳደሩና በነ ደብረፅዮን ቡዱን የተሾሙ ሁለት ከንቲባዎች እንዳሏት ይታወቃል።
በሰልፉ ላይ ከተማችን ለወራት ያለ ከንቲባ መቆየቷ አግባብነት የለውም፣ የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ውሳኔዎች ይከበሩ፣ የህዝባችንን አንድነት ለመሸርሸር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አጥብቀን እንቃወማለን፣ መንግስትን ለመገልበጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ይቁሙ፣የሚሉ ድምፆች ተስተጋብተዋል።
@ባላገሩቲቪ