በስልክ ቁጥራችሁ ሊፈጸም ከሚችል ወንጀሎች ተጠንቀቁ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አሳሰበ!
በተጠናቀቀው የበጀት አመትም በ130 ሺህ የኩባንያው ደንበኞች የመስመር ስልክ ላይ የማጭበርበር ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ኢትዮቴሌኮም አስታውቋል፡፡
በተጠቀሰው የማጭበርበር ወንጀል የተነሳ ደንበኞች ለአንግልትና ለወንጀል ድርጊት ተጠያቂነት እየተዳረጉ መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮ- ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ኩባንያውም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጸዋል።
የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል መከላከል እንዲቻል ደንበኞች በተለያየ አጋጣሚ የሞባይል ስልካቸው በሚጠፋበት ወቅት በአቅሪያባቸው በሚገኙ የሽያጭ ማዕከላት በማሳወቅና የስልክ መስመራቸውን በማዘጋት ምትክ ሲም ካርድ መውስድ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ደንበኞች የስልክ መስመራቸውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ባለመስጠትና ለወንጀለኞች ተባባሪ ባለመሆን በስልክ መስመራቸው አማካኝነት ከሚፈጸም ወንጀል እንዲጠነቀቁ ማሳሰባቸውን አስታውቀዋል፡፡
@Ab_Mustefa