ውሸትን እንጠንቀቅ!!
———
በተለይ እራሳችን ወደ ሰለፊይነት ያስጠጋን ሰዎችን በሐቀኝነት፣ ውሸት አጥብቀን በመጠየፍና በመጠንቀቅ ለሰዎች ጥሩ አርኣያ ልንሆን ይገባል!! የውሸትን ሀራምነትና ፀያፍነት የሚገልፁ የተለያዩ የቁርኣንና የሐዲስ ማስረጃዎች እጅግ በጣም በርካታ ናቸው። ይህ ከመሆኑም ጋር ግን አላህ ይጠብቀንና ብዙዎች በዚህ በሽታ ሲወድቁ ይስተዋላል፣ ይልቁንም ሰዎችን መልካም የሚያስተምሩ "አገሌማ አይዋሸም…" ተብለው የሚገመቱ ሰዎች በማይታሰብ መንገድ ውሸትና ያልተረጋገጠ ወሬ ሲያወሩ በሰማሀው ጆሮህ እስከማፈር ትደርሳለህ።
ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ረቢዕ ቢን ሃዲ'ል መድኸሊይ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
“በአላህ ይሁንብኝ አንድ ሰለፊይ ይዋሻል ብዬ አዕምሮዬ ላይ መቅረዝ አልችልም!። ለሚስት (በአንዳንድ ከአቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ ለማረጋጋት ሲባል) መዋሸት እንደሚፈቀድ አውቃለሁ፣ ነገር ግን አላደርገውም! ልዋሻት አልችልም። ለወንድ ልጅ (በአንዳንድ አስገዳጅ ሁኔታዎች ለቤተሰቡ፣ለሚስቱና ለልጆቹ) መዋሸት በስሱ የተፈቀደበት ሁኔታ አለ፣ ነገር ግን ወላሂ እኔ በቤተሰቤ ላይ ይህንም ቢሆን አላደርገውም። በእውነት ቢሆን እንጂ አልኗኗራቸውም። እኔ ቤተሰቦቼንም ልጆቼንም የማሳድገው በእውነት ነው፣ አልሀምዱ ሊላህ ምልክቱን (ውጤቱንም) እየተመለከትኩባቸው ነው። ተማሪዎቼንም የማንፀው፣ ሙስሊሙንም ማህበረሰብ በሙሃዶራዎቼና በኪታቦቼ የምመክረው በእውነተኝነት ነው። ከውሸት በማስጠንቀቅ!! በዲናዊና በዱኒያዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን አደገኝነቱንም አብራራላቸዋለሁ!!።” [አል-ፉሱል አል'ሙዲየህ ሚን ሲረቲ ሸይኽ ረቢዕ 146-147]
ይህ የሸይኽ ረቢዕ ንግግር ለሚገባው ትልቅ መልእክት አለው!! የአንዳንድ ሰዎች ሁኔታ በጣም ይደንቀኛል!፣ አይዋሸኝም ብሎ የሚያስባቸውን ሰው በማስረጃ እስኪይዛቸው አይን ያወጣ ውሸት ይዋሹታል፣ በማስረጃ ሲጋለጥ ደግሞ ለራሱ ከኪሱ አውጥቱ በሰጠው ፈትዋ ከዚህ ከዚህ አንፃር መስለሃ አለው ብዬ ነው ብሎ የሌባ አይነ ደረቅ… እንደሚባለው ድርቅ ሲል ይስተዋላል።
ውሸትን እንጠንቀቅ!! ውሸትን እንጠየፍ!!
https://telegram.me/IbnShifahttps://telegram.me/IbnShifa