Abu_Muawiya_As_Selefy (Channle)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ከቁርአንና ከሀዲስ ማስረጃ እስከሌለህ
ድረስ አቋም አትያዝ !
ለሁሉም ሰው ሂዳያን ተመኝለት
ሀቅን እንጂ ሰውን አትከተል።
"ሰው በሀቅ ይለካል እንጂ
ሀቅ በሰው አትለካም"!
https://t.me/abuumuawiya
https://t.me/abuumuawiya
ያለዎትን ሀሳብ በዚህ ይጠቁሙኝ
በተለይም ስህተት ከተመለከቱ
በአስቸኳይ ጠቁሙኝ።
@Abumuuawiya
@Abumuuawiya

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🟢መልእክት ለቁርኣን ቃሪኦች

*[ يا قارئ القرآن لاتكن من الذين يتعجلون بالقرآن ولا يتأجلونه]*

أخرج أبو داود في سننه عن جابر -رضي الله عنه- قال: خرج علينا رسول الله -صلى الله عليه وسلم- ونحن نقرأ القرآن، وفينا العربي والأعجمي، فقال: ((اقرءوا فكل حسن، وسيجيء أقوام يقيمونه كما يقام القدح يتعجلونه ولا يتأجلون)) 
صححه الشيخ الألباني في
الصحيحة(٢٥٩ )
والشيخ مقبل في الصحيح المسند(٢٣٦)

قال صاحب عون المعبود رحمه الله

*[ يقيمونه ]* أي يصلحون ألفاظه وكلماته ويتكلفون في مراعاة مخارجه وصفاته.

*[ كما يقام القدح]* أي يبالغون في عمل القراءة كمال المبالغة لأجل الرياء والسمعة والمباهاة والشهرة.

*[ يتعجلونه ]* أي ثوابه في الدنيا.

*[ ولا يتأجلونه ]* بطلب الأجر في العقبى بل يؤثرون العاجلة على اﻵجله ، ويتأكلون ولا يتوكلون. انتهى

*قال العلامة المحدث مقبل الوادعي* رحمه الله
وفيه علم من أعلام النبوة فقد كثر المتأكلون بالقرآن.


https://t.me/Menhaj_Alwadih


Forward from: Muhammed Mekonn
📌 إِنَّا لِلّهِ وَإِنَّـا إِلَيْهِ رَاجِعونَ  ጥንቃቄ

🔎 በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት የቴሌግራም ስሙን Allah ብሎ ለፃፈው ሰው የተወለደበት ቀን ሲደርስ It′s Allah′s  birthday today! ❨ዛሬ የአላህ ልደት ቀን ነው!❩ በሚል ወደተለያዩ ሰዎች ይላካል! ይህ ክህነት ለመሆኑ ከየትኛውም ሙስሊም አይሰወርም።

👉 የትኛውም ሙስሊም ሶላት ይሰግዳል። የሚከለክለውን ምዕራፍም በቃሉ ይሸመድዳል።

↩️ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
↪️ በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡»

↩️ اللَّهُ الصَّمَدُ
↪️ «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡»

↩️ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
↪️ «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡»

↩️ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ
↪️ «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»


👌 ያልወለደ እና ያልተወለደ እንዲሁም አንድም ቢጤ የሌለው ሀያል ጌታ አላህ የልደት ቀን የለውም። ግልፅ ክህደት መሆኑ ከማንም አይሰወርም

👉 በመሆኑም እናንተ ሙስሊሞች ሆይ ተጠንቀቁ በናንተ ሰበብ ይህ ክህደት እንዲሰራጭ ሰበብ ላለመሆን የቴሌግራም ስማችሁን በአላህ ስም አትፃፉ

👉 በተለይ ሴቶች ማንነታችሁን ለመደበቅ ሲባል ስማችሁን ከመፃፍ ይልቅ ሌላ ነገር ትጠቀማላችሁ። ይህ ጥሩ ነው።
ነገር ግን በአላህ ስምና ተያያዥ በሆኑ ቃላት መፃፍ የለባችሁም። መክፈቱ አስፈላጊ ከሆነ በባላችሁ ስም ክፈቱ! አለቀ

👉 ለምታውቁት ሁሉ ሸር (Share) በማድረግ አላዋቂዎችን ከጥፋት እንከልክል! እኔ በሁሉም ግሩፕ እና ቻናሎች እንዲሁም በግል Contacts እልካለሁ እናንተም ወደ ስራ!

📝 ወንድማችሁ አቡ ዒምራን

🏝 👉 🔎 👌 ➴➴➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/10087


🔵 ረመዳናዊ ግንዛቤ 1

🔵 ተቀባይነት ያለው አምልኮ

🔵 ጨረቃ መታየቱ በተለያዩ ሀገራት ቢለያይስ⁉️


✍ከሸይኽ ሁሰይን ሙሀመድ አስልጢይ ጠቃሚ መልዕክት ።

📚مجالس رمضانية
⏭⏭⏭ ይቀጥላል

🔊 አቡ ሀመዊየህ
https://t.me/Menhaj_Alwadih






✅ የእህታችን መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?

ክፍል ሁለት

እህታችን መዲና ህመሟ ወደ ሞት የተሳፈረችበት መጓጓዣ መሆኑን ስታውቅ ከልጆቿ ጋር የነበራትን ሁኔታ ቀየረች ። የመጀመሪያው ጠዋት ወጥቶ ወደ ተቀጠረበት ሱቅ ስለሚሄድ እቤት ብዙ አይገኝም ። ሁለቱ ልጆቿ አንዱ ወንድሞችን አስቸግሬ የአመት እንዲከፈልለት አድርጌ ሁለተኛውን ደግሞ ት/ቤቱን ስላለው ሁኔታ አስረድቼ እንዲቀበሉት አድርጌ እየተማሩ ነው ።
እነዚህ ልጆች ከእናታቸው ውጪ የሚያውቁት የለም ከት/ ቤት ሲመጡና በእረፍት ቀን ካጠገቧ ዞር አይሉዩም ።
እሷ አልጋ ላይ እነርሱ መሬት ላይ ሆነው ይተያያሉ ። እናት ለልጆቹ ተንሰፈሰፈ ሲባል የሷ አቻ የለውም ። የሆነ ሳአት ወጥተው ከተጫወቱ ይታጠቡ ልብስ ይቀየርላቸው ትላለች ። ቢያንስ በቀን ሁለቴ ታጥበው ልብስ ይቀየርላቸዋል ። በሳምንት ሁለቴ ገላቸው ይታጠባል ። ምግባቸው እሷ ሳታየው አይቀርብላቸውም ። የመጨረሻውዎቹ ሁለት ወሮች አካባቢ በልጆቿ ላይ ሁኔታዋን ቀየረች ።
ይህ የሆነው በሞት እንደምትለያቸው ስታውቅ ነበር ። አጠገቧ እንዳይቀመጡ ማድረግ ጀመረች ። ፊት ነሳቻቸው ታመናጭቃቸዋለች ። ይህን የምታደርገው ውስጧ እየተሰቃየ ስለያቸው እንዳይጎዱ ይጥሉኝ በሚል አሳዛኝ ውሳኔ ነው ። ምክንያቱ በማይገባቸውና በማያውቁት ሁኔታ የእናታቸው ሁኔታ የተቀየረባቸው ህፃናቱ ግን መሄጃ የላቸውምና ወደርሷው ነው የሚመለሱት ። ትስቅልን ይሆናል ታቅፈን ይሆናል በሚል ያዩዋታል ይቀርቡዋታል ይጠጉዋታል ። ሁኔታዋ ከእለት እለት እየተባባሰ ሁለመናዋ እየከዳት መጣ ። አይኗን መክፈት ያቅታት ጀመር ምላሷ በምትፈልገው መልኩ ማዘዝ አቃታት ። አጠገቧ ላሉ እህቶች እያቃሰተችና በተራ ተራ ፊደሎችን በትግል እያወጣች ለልጆቼ እናታችሁ አላህ ወስዷታል በሉዋቸው አለቻቸው ። መጨረሻ ላይ አላህ ሆይ ልጆቼን አደራ ብላ ከአላህ በኋላ የልጆቼን አደራ እኔን ለማዳን ለተሯሯጡ እህቶቼና ወንድሞቼ ሰጥቻለሁ ብላ በዱንያ ላይ ላታያቸው ትታቸው ወደ ማይቀረው አገር አኼራ ሄደች ።

ክፍል አንድን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/bahruteka/5731

https://t.me/bahruteka


🔷 የእህታች መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?
ክፍል አንድ

እህታችን መዲና ደምሴ ለሞቷ ሰበብ የሆነው የጡት ካንሰር እንደነበር እናውቃለን ። አላህ በሰው ልጆች ላይ የፃፈው ሞት ቅሮት የለውም ። ሳአቱን ጠብቆ ይመጣል ሰበብን ከሰበቡ ባለቤት ጋር እንዲገናኝ ያደረገው አላህ ለማንኛውም ሰው ሞት ሰበብ አድርጎለታል ። የእህታችንም ከዚህ የተለየ አልነበረም ።
ይሁን እንጂ ከሞት ሰበቦች ውስጥ አንዱ ህመም ነው ። የህመሙ አይነት በጣም ቢለያይም ሰዎች በተለያየ መልኩ ህመምተኛውን ከህመሙ እንዲድን ሰበብ ያደርሳሉ ። በሰበቡ እንዲድን አላህ የፈቀደው ይድናል ። አላህ በሰበቡ እንዲድን ያልፈቀደለትና ያ ህመም ለመሞቱ ሰበብ የሚሆነው በዛው ወደ አኼራ ይሄዳል ። ነገር ግን ሰበብ በማድረሱ ቤተሰብና ዘመድ ሰበብ አድርሰናል የአላህ ውሳኔ ነውና ምንም ማድረግ አንችልም ብሎ ይፅናናል ።
በጣም በሚገርም መልኩ ብዙ ቤተሰቦች ከቤተሰባቸው ሞት ይልቅ ሰበብ ባለማድረሳቸው ሁሌም ፀፀት ሆኖባቸው ይኖራሉ ።
ወደ እህታችን መዲና ስንመለስ በሽታዋ ካንሰር መሆኑ ከታወቀ በኋላ የሚቻለው ሁሉ ሰበብ ለማድረስ ሁሉም ተረባርቧል ። ቅስም የሚሰብረውና ውስጥን የሚያደማው ግን እህታችን የጡቷ ህመም ሲጀምራት ለመታየት ሐኪም ቤት ለመሄድ አቅም ማጣቷ ነው ።
እራሳቸውም ከህይወት ጋር ትግል ውስጥ ካሉት ወንድሞቿ አንዱን ጡቴን እያመመኝ ነው ሐኪም ቤት ለመታየት ትንሽ ሳንቲም ፈልግልኝ ብትለውም ወንድሟ ሊያገኝላት ባለመቻሉ ሳትታይ ትቀራለች ። የጡቷ ህመም ግን ስር እየሰደደ አቅሙን እያዳበረ ነበር ። አደጋው እያወቀችውና እየፈራችውም ግን ለማን ትንገር እህቶቿን ማስቸገር አልፈለገችም ከህመሟ ጋር ግብግብ ቀጥላ ቀናቶች ለሳምንታት ሳምንታት ለወራቶች ቦታ እየለቀቁ ህመሟ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ለአንድ እህቷ ትናገራለች ። እህት ደንግጣና ፈርታ ወደ ሀኪም ቤት ይዛት ትሄዳለች ስትመረመር የፈራችው አልቀረም በጣም ዘገያችሁ ወደ ካንሰርነት ተቀይራል ተባሉ ። የዚህን ጊዜ ነበር ጉዳዩ ወደኛ የደረሰው እንደምታውቁት ብዙ እህትና ወንድሞች ርብርብ አድርገው የሚቻለው ሁሉ ህክምና ተደርጎላት ነበር ። መጀመሪያ ሐኪም ቤት ለመሄድ 500 ብር ያጣችው እህታችንን ህይወት ለመታደግ እስከ 800, 000 ወጥቷል ።
እህታችን መዲና አላህ በጀነት የምታርፍ ያድርጋት እንጂ ህይወቷ በፈተና የተሞላ ነበር ። ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የነበረችው መዲና የትዳር አጓርዋ የሳንቲም ድህነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ነበር ማለት ይቻላል ። ብዙ ወንድሞች የተለያየ ከሸክም እስከ ሊስትሮ ከዘበኝነት እስከ ፅዳት ሰራተኝነት አነስተኛ ስራ እየሰሩ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ ። ይህ የሀላፊነት መሰማት ውጤት ነው ሀላፊነት የማይሰማው የሆነ አካል ችግር ሲመጣ ጥሎ ይጠፋል ። የመዲናም ባለቤት ከእነዚህ አንዱ ነበር ። በካንሰር ተይዛ ከካንሰሩ በላይ የልጆቿ ረሃብ በሽታ ሆኖ የሚያሰቃያትን ባለቤቱን ለመርዳት ከመጣር ይልቅ ጥሎ መሸሽ ነበር የመረጠው ። እናቱ ኬሞ ስትጀምር የሰውነቷ ፀጉር ሲረግፍ ያየው የመጀመሪያ ልጇ የ9 ጠኛ ክፍል ትምህርቱን ትቶ የእናቱን ሸክም ለመቀነስና ለማሳከም ሲል ሰው ቤት ተቀጠረ ። ‼
ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ በእናቱ ላይ ሌላ ሸክምና ህመም የሚጨምር ነበር ። ልጇ ከእድሜው በላይ ጫና ውስጥ ገብቶ ትምህርቱን ማቋረጡ ሌላ ህመም ሆነባት ። ህመሟ በወንድሞችና እህቶች እርዳታ ህክምና ጀምራ በተለይ ከውጭ ሀገር ይምጣ የተባለው መርፌ ከጀመረች በኋላ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ የነበረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ሁኔታው አስከፊ መሆን ጀመረ ። ሁለቱ ልጆቿ እድሜያቸው ገና ሲሆን ሶስተኛው አምስት አመቱ አካባቢ ነው ። እነርሱን እያየች ስታለቅሰ አጠገቧ እየተቀመጠ ጡትሽ ስለተቆረጠ ነው ወይ የምታለቅሺው አይዞሽ ይበቅላል ይላታል ። የእነዚህ ልጆቿ ሁኔታ ፊት ለፊቷ እያዘገመ እየመጣ ካለው ሞት የበለጠ እንደውጋት ቀስፎ እየያዛት በአካልና የውስጥ ህመም ውስጥ ሆነች ። ከቀናት በፊት ባለቤቴ ልትጠይቃት ሄዳ ሳለች በእንባዋ ትራሷ ርሶ አየች ምን ብላ ልታፅናናት እንደምትችል ግራ ገብቷት እያለ ትንሹ ልጇ እናቴ አትሙችብኝ ብሎ ያቅፋታል ። ከብዙ መረባበሽ በኋላ አላህዬ ያንተን ውሰኔ እቀበላለሁ ግን ለእነዚህ ልጄቼ ብኖር ደስ ይለኝ ነበር ብላ የበለጠ ተረብሻ ባለቤቴም የሚያፅናናት ሲያስፈልጋት ትታ ወጣች ።

https://t.me/bahruteka




.السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
.
በአይነቱ ለየት ያለና ደማቅ ፕሮግራም

➡️ ነገ ማለትም የካቲት 15/2017 E.C
🕰ማታ ከ 3:20 ጀምሮ በአዳማ ከተማ የአልፈትህ ወነስር የሰለፊዮች የመስጅድ ቦታ ግዢ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ላይ የሙሓደራና የኒያ ፕሮግራም
ተዘጋጅቶ ይጠብቀናል።

🪑 ተጋባዥ እንግዳችን

🎙የተከበሩ  ሸይኽ አቡዘር አላሕ ይጠብቃቸው

🔹 ሙሐደራው የሚደረግበት አድራሻ የሚከተለው ሲሆን 𝕛𝕠𝕚𝕟 ብለው ይጠብቁን !!!

https://t.me/adama_ahlusuna_weljemea


Forward from: مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)
ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

የፊታችን እሁድ በቀን 16/06/2017  ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም በመድረሳችን አልኢስላሕ ለየት ባለና ባማረ ሁኔታ እንኳን መቅረት በማርፈድ የሚያስቆጭ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል፡፡ 

ተጋባዥ እንግዶች፡-

1ኛ.   አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ኢብኑያሲን አልለተሚ (ሐፊዘሁሏህ)

2ኛ.   አሸይኽ ሐሰን ገላው (ሐፊዘሁሏህ)

3ኛ.   አሸይኽ ዩሱፍ አሕመድ (ሐፊዘሁሏህ)

በተጨማሪ ሎሎችም ኡስታዞች የሚገኙ ይሆናል፡፡

👌 በአሽይኽ ዓብዱልሐሚድ ኢብኑ ያሲን አልለተሚይ የሚሰጠው ወርሀዊ ፕሮግራማችን ከፊታችን ጁሙዓህ ከአስር ሰላት በኋላ ጀምሮ በተለመደው ሰአት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

አድራሻ፡-  አልኢስላሕ መድረሳ ፉሪ ኑሪ ሜዳ ባጃጅ  ተራ መጨረሻ

ሰዓት፡- ልክ 2፡30 ይጀምራል፡፡

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል!!!!!



የአልኢስላሕ መድረሳ👇👇👇   የተለያዩ ደርሶችን በቀጥታ ስርጭት ለመከታተል እና የሚለቀቁ ደርሶች ለማግኘት የመድረሳውን ቻናል #join በማለት ይቀላቀሉ። https://t.me/medresetulislah


Forward from: Muhammed Mekonn
ሌራ እንግዶቿን ለመቀበል በዝግጅት ላይ...

🌐 t.me/kedrAbuabderehman

ኑ ከመሻይኾቻችን ትክክለኛ እውቀት ተማሩ!

🚥 ሙሉ አድራሻ፦ በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ በስልጦ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በሌራ ከተማ በኢማሙ አህመድ ኢብን ሀንበል መስጂድና መድረሳ

https://t.me/AbuImranAselefy/9824


Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
🏝 ልዩ ሀገር አቀፍ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም

👉 በአላህ ፈቃድ የዲን ትምህርት ድግስ ከቀን 07/06/2017 የጁመዓ ኹጥባ እና ሶላት ጀምሮ  ለተከታታይ 3 ቀናቶች ተዘጋጅቷል።

 🏞 ቦታሌራ ከተማ በኢማሙ አህመድ መስጂድ እና መድረሳ ተሰናድቶ ይጠብቃችኋል።

🪑 በዝግጅቱ ላይ ከሚገኙ ውድና ብርቅዬ መሻይኾች መካከል፦
🎙 አሸይኽ ዐብዱልሐሚድ  ያሲን (ከለተሞ)
🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ሀያት (ከወሎ ሐራ)
🎙 አሸይኽ ሙሐመድ ጀማል (ከኮምቦልቻ)
🎙 አሸይኽ ሙባረክ አልወልቂጢይ (ከቀቤና)
🎙 አሸይኽ አብድል ከሪም (ከኦሮሚያ ጅማ)
🎙 አሸይኽ መህቡብ (ከሳንኩራ)     
🎙 አሸይኽ አህመድ ወሮታ (ከጎንደር)
🎙 አሸይኽ አወል (ከዳሎቻ)

በተጨማሪም በቀጥታ ስርጭት
🎙 አሸይኽ ሁሴይን መሀመድ (ከሳዑዲ አረቢያ)
🎙 አሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን (ከሳዑዲ አረቢያ)
🎙 አሸይኽ ሀሰን ገላው (ከባህር ዳር)
🎙 አሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ከባህር ዳር)

👉 እንዲሁም እንደ ኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ የመሳሰሉ በርካታ ኡስታዞች የሚታደሙበት ደማቅ ፕሮግራም ነው።

👉 ከሚሰጡ ኮርሶች መካከል፦
📚 شُروطُ الصَّلاةِ وَواجِباتُها وَأركانُها
📚 የሶላት መስፈርቶች ማዕዘናቶቿ እና ግደታዎቿ

📝 للشـيخ محمد بن عبد الوهاب النجدي
🎙 በሸይኽ አብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል`ለተሚይ
       
የሀቅ ወዳጆች ሁሉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል እንዳትቀሩብን!

ማሳሰቢያ፦ ሁላችሁም ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና የማታ ልብስ እንዳትዘንጉ።

አላህ ካለ ሩቅ ላላችሁ 𝙡𝙞𝙫𝙚 ላይ እናካፍላችኋለን
         ➘➘➘➘ 
https://t.me/AbuImranAselefy
https://telegram.me/IbnShifa

🔎 ሸር በማድረግ ለሰለፍዮች በሙሉ የማድረስ ሀላፊነታችንን እንወጣ


Forward from: مدرسة الإصلاح (አል ኢስላሕ መድረሳ)
🚎 ሀገር አቀፍ ታላቅ የዲን ኮንፈረንስ የፊታችን ጁመአ ጀምሮ በሚደረገው ፕሮግራም ላይ
ከአዲስ አበባ ብቻ መሳተፍ ለምትፈልጉ በነዚህ ስልክ ቁጥሮች በመደወል ፕሮግራም መያዝ ትችላላቹ

✅ ፉሪ ፣ ኬንቴሪ ፣ ሰበታ ለምትገኙ 0941058157

✅ አለም ባንክ ፣ ስልጤ ሰፈር ፣ ቤተል ለምትገኙ +251949435485

✅ መላው አዲስ አበባ ለምትገኙ

+251936985302


👉 ማሳሰቢያ ቀለል ያለ የማደሪያ ልብስ መታወቂያ መያዣቹን አትርሱ

🔴 የመነሻ ሰአት ጁመአ ከቀኑ 3 :00 ይሆናል

https://t.me/medresetulislah


ታላቅ የምስራች በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ ታላቅ የሙሓደራ ድግስ በአዳማ ከተማ



    እነሆ የፊታችን እሁድ የካቲት 2/2017 በአዳማ ከተማ 03 ቀበሌ በመደረሰቱል ፈትህ ወነስር ልዩ የሙሐደራ እና ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።

     የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች : –

①ታላቁ እና ተወዳጁ ዶ/ር ሸይኽ ሑሰይን ብን ሙሐመድ አስልጢይ (ሀፊዘሁሏህ)

②ተወዳጁ ዳዒ ኡስታዝ ሻኪር ሱልጣን (ሀፊዘሁሏህ)
  
በአሏህ ፍቃድ ሌሎችም ይኖራሉ

     ፕሮግራሙ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2 : 30 የጀመራል ። 

https://t.me/adama_ahlusuna_weljemea






Forward from: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
الواضح_في_تيسير_منهج_السلف_الصالح.pdf
3.3Mb
👉 አዲስ ኪታብ pdf የገፅ ብዛት 313

عنوان:- الواضح في تيسير منهج السلف الصالح
የደጋግ ቀደምቶችን መንገድ ገር በሆነ መልኩ ግልፅ ማድረግ
للشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد بن عبد الله الإتيوبي السلطي حفظه الله

✍🏻አዘጋጅ:- ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ዐብደላህ አስ-ስልጢ (ሀፊዘሁላህ)

(ዐረቢኛ የምትችሉ pdf ን አውርዳችሁ አንብቡት፣ የምታቀሩም አቅሩት)

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://t.me/HussinAssilty
https://t.me/HussinAssilty


👆👆👆
🔈
#በተቻለ መጠን ከንቱን የማውገዝ ግደታነት

🔶
በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ በቅልጦ  ወረዳ በሾሞ ቀበሌ የተደረገ ሙሐደራ ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

📌 ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
🌐 https://t.me/shakirsultan




Forward from: ኢብኑ ፈቂር ( ሳዲቅ አወል)
መጅሊስ እየፈጠረው ያለው በሱና ወንድሞችና ኮሚቴዎች የጅምላ እስር  በቅበት ከተማ አስተዳደር

✔️ ነገሩ እንዲህ ነው:–
        ራሱን የሀገሪቱ መንግስት አድርጎ የተመለከተው የቅበት ከተማ አስተዳደር መጅሊስ ተብዬ ሰሞኑን በከተማው ውስጥ በምትገኝ ኣንዲት የሰለፊያ መስጅድ ውስጥ ረብሻና ብጥብጥ አለ እያሉ ሰላማዊ በሆነው ጀመዓ መሃከል አለመግበባት እንዲፈጠር ቀሰቀሱ።

        ከዛም ችግሩን ኮሚቴውና የቀበሌ መጅሊስ በውይይት ይፍቱት በሚል ለውይይት ተቀመጡ፣ ተበደልኩ ያለ ሰው አለ ብለው ስለነበረ ኮሚቴዎች ምንድነው? በማለት ጠየቁ፣ ለጥያቄውም መልሱ መስጅዳችን ሰላም ነው፣ ቂርዓትም ስርዓቱን ጠብቆ ቁርዓንንና ሀዲስን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተካሄደ እንዳለ ተናገሩ።



      ☑️በመቀጠልም ለሚያነሱት እዚህግባ ለማይባለው ወሬ በአግባቡ መልስ ተሰጠ፣ በመቀጠል ለውሳኔ ሁለት ቀን ተብሎ ተሰጠና ዝምምምም ኣሉ እስከ 10 ቀን ከዛም የመጅሊስ አካላት የኔ አመለካከት ብለው የያዙት እቅድ ስላላቸው የሆነ ረብሻን ይፈልጉ ስለነበረ በሰላማዊ ዳዕዋ ላይ የማይክ መቆጣጠሪያ ብሬከር እንዲመልስ ኣንድን ተላላኪ አደረጉ ።

     በዚህ መሃል በጀመዓ ፊት ደዕዋን ለማወክ ሞከረ አስቆመ፣ በነጋታው አስር ከተሰገደ በኋላ መጅሊስ በመነሳት በዛው መስጅድ የመጀመሪያውን ኮሚቴ አውርደናል እያለ  አዲስ ኮሚቴን ማንበብ ጀመረ ።

   በንዲሁ አንዳለ ጀመዓው እድል ስጡን ምንድነው የተፈጠረው? ኮሚቴን መምረጥ ሀላፊነቱ የማን ነው? ብሎ ጥያቄ ለማንሳት እድል ለመስጠት አልፈለገም።


የጀመዓውን ሀሳብ ላለመስማት ቶሎ ብሎ  ጥሶ ወጣ፣ ጀመዓው የናንተው ኮሚቴው እኛን አይወክሉም በማለቱ ነባር ኮሚቴዎችን ፣ ኡስታዞችን እንዲሁም ጀመዓውን ከእሁድ ቀን  ጀምሮ በፖሊስ እስር ቤት እያፈሱ ይገኛሉ።


      ይህ ሁሉ ድርጊት ሲፈፀም ተበዳዩ ኮሚቴና ጀመዓ ሆኖ ሳለ መጅሊስ የሱን አመለካከት በግድ ለማስገባት በሚል ንፁሃን ጀመዓን ለእንግልት እየዳረጉ ይገኛሉ። ለመሆኑ የመጅሊስ ፍላጎት ምን ይሆን??……………








         https://t.me/sadikawol

20 last posts shown.