Forward from: Bahiru Teka
✅ የበላይነት በፅናት እንጂ በብዛት አይደለም ።
በአሁኑ ጊዜ ኢኽዋኖች ብዛትና አቅም ስላላቸው ከእርነሱ ማስጠንቀቅ ይከብዳል ይላሉ ። እነዚህ ሰዎች ውስጣቸው ያለው ሱና ደክሞባቸው በራሳቸው ጊዜ የተሸነፉ ናቸው ። ምክንያቱም አላህ ዓለምን ከጨለማ ያወጣው በአንድ ነብዩ ነው ። ዐለሙ አቅም በነበራቸው ከሀዲያን ተጥለቅልቆ ሳለ ።
ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሞቱ ጊዜ አብዛኛው ኢማን ሰርፆ ወደ ልቡ ያልገባ የገጠሩ ህዝብ ወደ ኩፍር ሲመለስ ዲኑ የተጠበቀው በአቡ በከር ፅናት ነበር።
የሙዕተዚላዎችም ቁርዓን ፉጡር ነው የሚለው ፈተና በኢማሙ አሕመድ ፅናት ተወግዶ አላህ ሱናን የበላይ አደረገው ። ይህ እንግዲህ ሙዕተዚላዎች ከነበራቸው አቅም ጋር ነው ።
እነደዚሁ አላህ ሱናን በሸይኹል ኢስላም ፅናት ከሞንጎሊያዎች ፣ ከሺዓዎች ፣ ከአሻዒራና አምሳዮቻቸው ፈተና ጠብቆታል ።
አሁንም በሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዓብዱል ወሀብ ፅናት ዱኑን እንዴት ህያው እንዳደረገው ለአሁኑ ትውልድ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው። ታድያ እነዚህ ሰዎች ብዙ ሆነው ሳይሆ ተዓምር የሰሩት በአላህ እርዳታ ታግዘው በነበራቸው ፅናት ነው ።
እኛም በሱና ላይ ፀንተን ለሱና ዘብ ከቆምን የአላህ ርዳታ ታክሎበት ሱናን የበላይ ማድረግ እንችላለን ሜዳ ውስጥ ሳንገባ ተሸናፊ አንሁን ።
https://t.me/bahruteka