እናት ፓርቲ በመንግስት ላይ መስርቶ የነበረውን ክስ ማሸነፉን ገለጸ
ዓርብ ጥር 9 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር "ሕገ ወጥ መኾኑን" በመግለጽ እናት ፓርቲ ክስ መመሥረቱ ይታወሳል።
ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ዛሬ ጥር 9 ቀን 2017 ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ ሚያዝያ 3 ቀን 2015 የወጣውና "ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ሲል መወሰኑን እናት ፓርቲ አስታውቋል፡፡
እንዲሁም መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ፓርቲ ገልጿል።
በተመሳሳይ በመዲነዋ የቤት ባለንብረቶች ላይ የተጣለው የንብረት ግብር ወይም የጣሪያና ግድግዳ ግብር ሕዝባዊ ቅሬታ ከቀረበበት በኋላ፣ የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር በከተማ አስተዳደሩ ላይ የሕግ የበላይነት ጥያቄ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማኅበር የሕዝብ ቅሬታ እየቀረበበት ባለው የአዲስ አበባ ከተማ የቤት ግብር ማሻሻያ ላይ ማብራሪያ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለከተማዋ አስተዳደር ያስገባ ሲሆን ማኅበሩ ቅሬታውን ያቀረበው በጉዳዩ ላይ ጥናት ካደረገ በኋላ እንደነበር አይዘነጋም፡፡