ብናልፍ አንዷለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው በመሾም ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤና የሥራ መመሪያ ተቀበሉ
ዓርብ ጥር 23 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለአምባሳደር ብናልፍ አንዷለም የሥራ መመሪያ በሰጡበት ወቅት፤ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ግንኙነት የሚመጥን ትጋትና ቁርጠኝነት የተላበሰ አመራር መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንቱ "የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆኖ መሾም የኢትዮጵያን ሕዝብና መንግሥት ሃላፊነትና አደራ መጎናጸፍ ነው" ብለዋል።
ኢትዮጵያና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የረጅም ዘመን ግንኙነትን የሚያጠናክር ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል።
በተጨማሪም አሜሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባት ሀገር በመሆኗ፤ በኢትዮጵያ ልማትና እድገት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አምባሳደሩ ጠንካራ ስራ ማከናወን እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።
በመሆኑም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም አሜሪካ ትልቅ እሳቤን የሚጠይቅ ዲፕሎማሲ የሚከናወንባት መሆኑን ታሳቢ ያደረገ አመራር እንዲሰጡም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ ወዳጅን ማብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም ገልጸዋል።