ዐቢይ በምክክሩ መዝጊያ መድረክ ለምን አልተገኙም?
ቅዳሜ፣ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በተጠናቀቀው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ አለመገኘታቸውን አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።
ዐቢይ፤ ይህ ኮሚሽን በወርሃ ታህሳስ 2014 ዓ.ም አዋጅ ጸድቆለት፣ በዚያው ዓመት በየካቲት ወር ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ፤ የመንግስታቸውን፣ የፓርቲያቸው ብልጽግናን አቋም ሲያንጸባሩቁ ቢከርሙም፣ ዛሬ በማጠናቀቂያው ግን አልተገኙም።
በዚህ መድረክ፣ የቀደሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንትና የአፍሪካ ህብረት የቀንዱ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንትና የፕሪቶሪያ ዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት አደራዳሪ ቡድን አባል ኡሁሩ ኬንያታ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድር፣ ከንቲባዎችና ባለሥልጣናት ቢታደሙም ዐቢይ ግን በመርሐ ግብሩ ተገኝተው ንግግር አላደረጉም።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን አለመገኘት በተመለከተ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎትም ሆነ ጽ/ቤታቸው አልያም ሌላ መንግስታዊ አካል፤ ቢያንስ ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ያሉት ምንም ነገር የለም።
በተረጋገጡትና ሚሊየኖች በሚከታተሏቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸውም፣ የሀገራዊ ምክክሩን መዝጊያ መርሐ ግብር በተመለከተ ምንም አላሉም።
ይህ ብቻ ሳይሆን በእነዚሁ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ገጾቻቸው፤ መልዕክት ካሰፈሩ 10 ቀናት ተቆጥረዋል።
እሳቸው በማጠናቀቂያ መድረኩ ባይገኙም፣ መንግስታቸውም ያልታደሙበትን ምክንያት ባይገልጽም እናንተ የአዲስ ማለዳ ተከታታዮች ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተገኙበት ምክንያት በተመለከተ ያላችሁን አስተያየታችሁን ብታሰፍሩልን ደስ እንሰኛለን።
ከዚህ በተጨማሪ ያለፈው አንድ ወር የምክክር ጉባኤውንና አጠቃላይ የኮሚሽኑን የሥራ ሂደት በተመለከተ ያላችሁን አስተያየት እንድታሰፍሩልን በትህትና እንጠይቃለን።
ዐቢይ ለምን አልተገኙም?፤ የምክክሩን ሂደትስ እንዴት አገኛችሁት? ጻፉልን!
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA