በኢትዮጵያ ቀናቸዉ ሳይደርስ የሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት ቁጥር በዓለም ላይ ከፍተኛ ከሆነባቸው አምስት ሀገራት አንዷ መሆኗ ተገለጸ
ሐሙስ፣ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ)
በኢትዮጵያ ቀናቸዉ ሳይደርስ የሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት ቁጥር በዓለም ላይ ከፍተኛ ከሆነባቸው አምስት ሀገራት ማለትም ከቻይና፣ ህንድ፣ ናይጄሪያና ፓኪስታን መካከል አንዷ መሆኗ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸዉ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር በአለም አቀፍ ደረጃ ለአስራ ስድተኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለአስራ ሶስተኛ ጊዜ በሚከበረዉ የመወለጃ ጊዜያቸዉ ሳይደርስ የሚወለዱ ህጻናት ቀን ታሳቢ በማድረግ “ለጨቅላ ህጻናት ክትትል እና የወደፊት ህይወትና አቅም በመሆኑ መዋእለ ነዋይ ይመድቡ በሚል” መሪ ቃል ባዘጋጀዉ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር ላይ ነዉ፡፡
የአለም የጤና ድርጅት እ.አ.አ 2020 ላይ በሰራው ጥናት መሰረት በአለም ላይ በአመት ከ13.4 ሚሊዮን ህጻናት ከመውለጃ ጊዜያቸዉ ማለትም ከ37 ሳምንታት ቀድመዉ እንደሚወለዱና በኢትዮጵያ ደግሞ 496ሺህ ህጻናት ቀናቸዉ ሳይደርስ እንደሚወለዱ በመድረኩ ተነሰቷል፡፡
ከሚወለዱት ህጻናት ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነዉ ያለቀኑ የሚወጣ ውልጃን መከላከል እንደሚቻል በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያ ያለዉ ቁጥር በመቶኛ ሲገለጽም 12.9 መቶ ሲሆን ይህ በአለም አቀፍ ደረጃ ካለው አማካኝ 9.9 መቶ የላቀ ነዉ ተብሏል፡፡
ህጻናት ያለ እድሜአቸዉ የሚወለዱበት አንድ ምክንያት ባይኖረዉም የአኗኗር ዘይቤ ፣ በቂ ያልሆነ ማህበራዊና የጤና ስርዓት አለመኖር እንደምክንያት ተነስተዋል። በኢትዮጵያ ያለ ጊዜቸዉ የሚወለዱ ህጻናት ቁጥርን ለመቀነስ በሆስፒታሎችን ያለዉ ዝግጁነት አናሳ መሆን፣ የህክምና መሳሪያዎች በሚፈለገዉ ልክ አለመኖርና ህጻናቱ ከተወለዱ በኋላ የሚሰጥ ድጋፍ ደካማ መሆን ደግሞ እንደተግዳሮት ተጠቅሰዋል፡፡
በአለም ደረጃ ቀናቸዉ ሳይደርስ ከሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት አብዛኛዉ ከሰሀራ በታች በሚገኙ ሀገራትና በደቡብ እስያ ሀገራት የሚመዘገብ ሲሆን 90 በመቶ የሚሆኑት ያለ ጊዜያቸዉ የሚወለዱ ጨቅላ ህጻናት ሞት ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸዉ ሀገራት እንደሚመዘገብ ተጠቅሷል፡፡
በኢትዮጵያም እ.አ.አ 2024/2025 ከተወለዱ 1000 ህጻናት ዉስጥ 25 የህጻናት ሞቶት የተመዘገበ ሲሆን ከዛ ዉስጥ አንድ ሶስተኛዉ የሚሆነዉ ካለጊዜያቸዉ የተወለዱ ህጻናት ሲሆን ጤና ሚንስቴር በ2030 የህጻናት ሞትን ከ25 ወደ 12 ለማዉረድ እንደሚሰራ ገልጿል፡፡
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲t.ly/mxA