አሐዱ፡ባንክ “ባይነሪ ቴክኖሎጂስ - ቢዩ ዴሊቨሪ (Beu Delivery) “ ከተሰኘ ተቋም ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ከተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማ መሆን የቻለው እና “ከብዙዎች ለብዙዎች” በሚል መርሁ የሚታወቀው አሐዱ፡ባንክ ተደራሽነቱን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ሰጪ ተቋምነቱን ለማሳደግ ያስችለው ዘንድ ከተለያዩ ተቋማት ጋር አብሮ መሥራት የሚያስችለውን የጋራ የመግባቢያ ስምምነቶችን በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡
አሐዱ፡ባንክ በዚሁ መሠረት ኅዳር 12 ቀን 2017 ዓ᎐ም የተለያዩ ትኩስ ምግቦችን ደንበኞች ባሉበት በቅልጥፍና እና በታማኝነት ለሕብረተሰቡ በማድረስ ከሚታወቀው ከባይነሪ ቴክኖሎጂስ ( “ቢዩ ዴሊቨሪ ፤Beu Delivery)” ከተሰኘ ተቋም ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ፈርሟል።ስምምነቱን የፈረሙት የአሐዱ፡ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰፊዓለም ሊበን እና “የባይነሪ ቴክኖሎጂስ “ ቺፍ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ አደም አብደላ ናቸው።
በስምምነቱ ላይ አቶ ሰፊዓለም ሊበን እንደገለጹት፤ ባንኩ ዘመኑን በዋጁ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶቹ በመታገዝ እንደ ቢዩ ዴሊቨሪ “(Beu Delivery) “ ካሉ ቴክኖሎጂን መሠረት ካደረጉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ደንበኞቻቸው ጋር በተመሳሳይ አብሮ የመሥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች
የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
👉https://linktr.ee/Ahadu_Bank