✔️ ኢዕቲካፍ(إلإعتكاف)
እውን ከሶስቱ(ከ3ቱ) መስጂዶች(ከመስጂደል ሐረም መካ፣ ከመስጂደ ነበዊ መዲና እና ከአቅሷ ቁድስ ፍልስጤን) ውጪ ኢዕቲካፍ ተደንግጓልን????
⬅️《وَلا تُباشِروهُنَّ وَأَنتُم عاكِفونَ فِي المَساجِدِ تِلكَ حُدودُ اللَّهِ فَلا تَقرَبوها كَذلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ آياتِهِ لِلنّاسِ لَعَلَّهُم يَتَّقونَ》
📚سورة البقرة(187)
↪️《መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ተቀምጣችሁ ባለቹበት ለሚስቶቻቹህ ተቃራኒ ፆታዊ እንክብካቤ አታድርጉላቸው ይህ የአላህ የክልክልነት ወሰን ነውና እንዳትዳፈሩት(እንዳትሻገሩ)።
አላህ አንቀፆችን በዚህ መልኩ የሚያብራራላቹህ እንዲትጠነቀቁት(እንድትፈሩት) ነው።》
📚ሱረቱል በቀራ(187)
⬅️عن حذيفة رضي الله عنه
↪️ሁዘይፋህ ኢብኑል የማኒ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና
⬅️قال رسول الله ﷺ:
↪️ነብዩ ﷺ ………
⬅️《"لا اعتكاف إلا في المساجد الثلاثة . المسجد الحرام, والمسجد النبوي, والمسجد الأقصى, 》
↪️ከሶስቱ መስጂዶች ማለትም መካ ከሚገኘው ከመስጂደል ሀረም፣መዲና ከሚገኘው ከመስጂደነበዊይ እና ፍልስጤን ከሚገኘው ከመስጂድል አቅሷ ውጪ ኢዕቲካፍ የለም።》ብለዋል።
📚أخرجه الطحاوي والإسماعيلي والبيهقي بإسناد صحيح عن حذيفة ابن اليمان رضي الله عنه، وهو
مخرج في "الصحيحة" رقم ٢٧٨٦،
📚ይህን ሀዲስ ኢማሙል በይሀቂይ በጠንካራ(በሰሒሕ) ደረጃ ሲዘግቡት፣
📚ኢማሙ ጣሃዊያህ እና ኢስማዒሊይ በጠንካራ(በሰሒሕ) ደረጃ ዘግበውታል።
⬅️مع الآثار الموافقة له مما ذكرنا أعلاه، وكلها صحيحة
↪️ሌሎችም የዚህን ሀዲስ ትክክለኝነት የሚደግፉ የቀደምቶች(የሰለፎች) ገለፃና ጥቆማ ያለ ሲሆን
📚 السلسة الصحيحة ٢٧٨٦.
📚ኢማሙ አልባኒ ይህን ሀዲስ ሲልሲለቱ አሰሒሐህ ሐዲስ ቁጥር(2786) ላይ
ጠንካራ(ሰሒሕ) ሐዲስ ነው ብሎታል።
⬅️ قال العلامة الإمام الألباني -رحمه الله-:
↪️ኢማሙ አልባኒይ አላህ ይዘንላቸውና ከዚህ ሐዲስ በመነሳት…
⬅️المساجد التي يُعْتَكَفَ فيها
➡️ኢዕቲካፍ ስለሚቻልባቸው(ስለተደነገገባቸው) መስጂዶች ሲያብራሩ…
⬅️وقفت على حديث صحيح صريح يخصص "المساجد" المذكورة في الآية -«ولا تباشروهن وأنتم عاكفون في المساجد»-(١) بالمساجد الثلاثة: المسجد الحرام, والمسجد النبوي, والمسجد الأقصى, وهو قوله ﷺ:
"لا اعتكاف إلا في المساجد الثلاثة"(٢)
➡️《ቁርአን ላይ መስጂዶች በሚል የመጣው ኢቲካፍ የሚቻልባቸው መስጂዶች በዚህ የነብዩ ﷺ ጠንካራ(ሰሂህ) ሀዲስ ሚተሮገም በመሆኑ ኢዕቲካፍ የተደነገገላቸው መስጂዶች ሶስቱ መስጂዶች ማለትም መካ የሚገኘው ካዕባህ የሚገኝበት መስጂልሀረም፣መዲና የሚገኘው የነብዩ ﷺ መስጂድ)መስጂዱ ነበዊይ እና ፍልጤን ቁድስ ከተማ የሚገኘው መስጂደል አቅሷ ብቻ ናቸው።》
⬅️وقد قال به من السلف فيما اطلعت حذيفة بن اليمان, وسعيد بن المسيب, وعطاء, إلا أنه لم يذكر المسجد الأقصى,
➡️ይህንን ኢዕቲካፍ በሶስቱ መስጂዶች ብቻ የተደነገገ መሆኑንና ከሶስቱ መስጂዶች ውጪ የሌለ መሆኑን ከቀደምቶች(ከሰለፎች) ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ ፣ ዓጣእ እና ሌሎችም የተቀበሉት ሲሆን
➡️ከዚህ ዘመን ሙስሊም ሙሁራን ደግሞ አቡ ኡሳማህ ሰሊም ዒዲኒል ሒላሊይ ይገኙበታል።
⬅️وقال غيرهم بالمسجد الجامع مطلقا, وخالف آخرون فقالوا: ولو في مسجد بيته.
➡️《ሌሎች ይህን ሀዲስ ባለመቀበል በማንኛውም ጀማዕ በሚሰገድበት መስጂድ ውስጥ ኢዕቲካፍ ይቻላል ያሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ቤታችን ውስጣ ባለች መስጂድ(መስገጂያ ስፍራ(ሙሰላ) ውስጥ እንኳን ይቻላል።》 ብለዋል።
⬅️《ولا يخفى أن الأخذ بما وافق الحديث منها هو الذي ينبغي المصير إليه, والله سبحانه وتعالى أعلم.》
➡️በመሆኑም ይላሉ ሸይኽ አልባኒ ➡️《ከነብዩ ﷺ ሒዲስ ጋር የሚስማማው አባባል ኢዕቲካፍ በሶስቱ መስጂዶች ማለትም በመስጂደል ሀረም፣በመስጂደ ነበዊይ እና በመስጂደል አቅሷ ብቻ የተደነገገ መሆኑ ስለሆን ራስን በነብዩ ﷺ ሀዲስ ላይ መግታት ተገቢ ነው።》ብለዋል።
⬅️《من رأى أنه لااعتكاف إلا في ثلاثة مساجد :
عن عبد الرزاق عن الثوري عن واصل الأحدب عن إبراهيم قال جاء حذيفة إلى عبد الله فقال الا أعجبك من ناس عكوف بين دارك ودار الأشعري قال عبد الله فلعلهم أصابوا وأخطأت فقال حذيفة ما أبالي أفيه أعتكف أو في بيوتكم هذه إنما الاعتكاف في هذه المساجد الثلاثة مسجد الحرام ومسجد المدينة والمسجد الأقصى وكان الذين اعتكفوا فعاب عليهم حذيفة في مسجد الكوفة الأكبر》
➡️ሁዘይፈተል የማኒ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ዘንድ በመምጣ
➡️《በአንተና በአቡል ሀሰነል አሽዓሪይ መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ የገቡ ሰዎችን እንዴት ዝም ትላለህ ነብዩ ﷺ ከሶስቱ መስጂዶች ከመስጂደልሀረም፣ከመስጂነበዊይ እና ከመስጂደልአቅሷ ውጪ ኢዕቲካፍ የለም እንዳሉ እያወክ ሲለው ዓብደላ ኢብኑ መስዑድም አንተ ዘንግተህ እነሱ ደግሞ አስታውሰው ከሆነስ በማለት መልሶለታል።》
➡️ሌላው መታወቅ ያለበት ነገር ነብዩ ﷺ ከመስጂደነበዊይ(ከመዲና መስጂድ) ውጪ ኢዕቲካፍ አልገቡም ነበር።
📚 من سلسلة الهدى والنور
📚ምንጭ:
📚ሲልሲለቱልሁዳ ወኑር
📚للعلامة المحدث الشيخ الألباني -رحمه الله-
سئل عن الاعتكاف وأين يكون؟
الصوتية على الرابط:
👉ለበለጠ መረጃ ሼኽ አልባኒ ኢዕቲካፍ የት የት መስጂድ መግባት እንደሚቻል የገለፁበትን ድምፅ ቀጥሎ አለሎትና ያድምጡ
✍አቡ ኢብራሂም
ሚያዚያ 03/08/2015 ዓ ው
ረመዷን 20/09/1444 ዓ ሂ
http://telegram.me/abuibrahim0102030405📚
http://www.alalbany.net/alalbany/audio/484/484_04.mp3